የህወሐት መነሻ አድዋ ያለው ኃይል መሰበሩ የጁንታው አከርካሪ መበጠሱን እንደሚያሳይ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አስታወቁ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር  መከላከያ ሠራ…

የህወሐት መነሻ አድዋ ያለው ኃይል መሰበሩ የጁንታው አከርካሪ መበጠሱን እንደሚያሳይ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አስታወቁ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር መከላከያ ሠራ…

የህወሐት መነሻ አድዋ ያለው ኃይል መሰበሩ የጁንታው አከርካሪ መበጠሱን እንደሚያሳይ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አስታወቁ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር መከላከያ ሠራዊቱ የሚቀረው ከጉድጓድ ውስጥ ያለውን ጁንታ አውጥቶ ለሕግ ማቅረብና ሙሉ በሙሉ አካባቢውን ነጻ ማድረግ መሆኑንም የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አስታውቀዋል፡፡ ትህነግ በምዕራብ ግንባር ድል እየሆነ እየሸሸ ነው፡፡ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ሀይል አባላትና ምኒሻ ትናንት እና ዛሬ ወሳኝ የሚባሉ አክሱም፣ አድዋና አዲግራትን አስለቅቋል፡፡ ባደረገው ኦፕሬሽንም በርካታ የጁንታውን ታጣቂ ኃይል ማርኳል፤ ደምስሷልም፤ የትህነግ በርካታ ኃይል ተመትቷል፤ በርካታውም እጅ ሰጥቷል፡፡ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ እንደገለፁት ነጻ የወጡት አካባቢዎች ለተኩስ የማያመቹ፣ ትልልቅ የልማት ተቋማት ያሉባቸው፣ በርካታ የሕዝብ ቁጥር የሰፈረበትና ወደ መቀሌ በተለያዬ አቅጣጫ ለመሄድ የሚያስችሉ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡ በጁንታው መንጋጋ የነበሩትን ቦታዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፈልቅቆ ማውጣቱ ለቀጣይ ድል ወሳኝ ናቸውም ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply