የህወሓትና የኦነግ የኢኮኖሚ አሻጥር እንመክት!!! ሚሊዮን ዘአማኑኤል

<<ሕይወት ማለት መብላትና መጠጣት፣ አዳዲስ ልብስ እያፈራረቁ መልበስ፣ ከባንክ ገንዘብ ማጠራቀም፣ አዲስ ‹‹ሞዴል›› መኪና ምንዳት፣… ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ በቀላሉ መንገድ ሊገኝ እንደሚችል አይተናል፡፡ ስብአዊ ክብር ግን በገንዘብ አይገዛም፡፡ ሐሪሶት (culture) የሌለው ሰብአዊ ክብር ምን እነደሆነ ማወቅ አይቻልም፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያጋጠመው ዋና ፕሮብሌም ነው፡፡>> ብርሃኑ ድንቄ

ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የጦር አበጋዞች መንግስት ወደ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ)  የጦር አበጋዞች መንግስት  በትረሥልጣኑን ለማራዘም ያሸጋገረበት የቅርብ ጊዜ ትዝታ በሽንፈት ተጠናቆል፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተስፋ ባለመቁረጥ አሁን ደግሞ ከመቐሌ ምሽጉ ስፖንስር በሚያደርገው ገንዘብና መሣሪያ ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የጦር አበጋዞች መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለይ በወለጋ፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ወዘተ ትጥቅና ስንቅ በማቅረብ ሠላም በማደፍረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ህወሓት  የዶክተር አብይ አህመድን አዲሱን ለውጥ ለማደናቀፍና በመላ ሃገሪቱ የሽብር ሴራ በመዘርጋት የዴሞክራሲውን መንገድና ነፃነት በመፈታተን ላይ ይገኛል፡፡ በሃገሪቱ የህግ የበላይነት ስለሌለ፣ ትላንት የፈፀሙትን ወንጀል ዛሬ ደግመውታል፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች በህግ ተጠያቂ ከሆኑ፣ የህዝብ ግጭቶችን በእንጭጩ መቅጨት ይቻላል እንላለን፡፡ ህወሓት የሶህዴፓ አብዲ ዒሊ የጦር አበጋዝ መንግሥት ሽንፈት በሆላ አዲስ ያገኘው መጋዣ የኦነግ ዳውድ ኢብሳ የሚመራ የፊንፊኔ የጦር አበጋዝ መንግሥት ጋሻ ጃግሬነት የተሰባሰቡት የሥልጣን ሱሰኞች በአሳዛኙ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ሃላፊ ጁሃር መሃመድ አንደበት የኦሮሞንና የኢትዮጵያን ደሃ ህዝብ ደም በማፋሰስ ላይ ናቸው፡፡ የኦነግ የጦር አበጋዞች በዘር ግንድ ላይ የተመሠረተ የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም፣ ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ስም፣ በዘር የተደራጀ ጦር በማሰልጠንና በመገንባት ሌላውን ዘር በማግለል የራሳቸውን ግዛትና መንግሥት በሌላው ላይ ለመጫን የተደራጀ ኃይል ያቆቁማሉ፡፡ የኦነግ  የጦር አበጋዞች  ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን ኦነግ በወለጋ መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠት   ማዕከላዊውን መንግሥት በመፈታተን ላይ ይገኛል፣ በቃህ ሊባል ይገባል እንላለን፡፡የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር በ1983 ዓ/ም የሽግግር መንግሥት ከወያኔ ጋር በመመሥረት በጊዜው በደኖ፣ አርባጉጉ፣ ወዘተ ህዝብ ላይ ያደረሰው የዘር ፍጅት ተጣርቶ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ አለመደረጉ ዛሬ ኦነግ በሃገሪቱ ውስጥ ወንጀል ለመስራት የተላላኪ ሚናውን በመወጣት ላይ ይገኛል ስለዚህ ከሁሉ በፊት የህግ የበላይነት መከበር ይኖርበታል እንላለን፡፡ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ሃላፊ ጁሃር መሃመድ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት በሥራ አስፈፃሚው መንግሥት የቀረበለትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቆቆሚያ ረቂቅ አዋጅን በመቃወም ከህወሓት ጋር ህብረት ፈጥሮል፡፡ ባለፈው ጁሃር መሃመድ በአዲስ አበባ ተገደሉ ያላቸው የ43 ኦሮሞ ሞቶች የስም ሊስት ውሽት በህግ ሳይጠየቅና በህግ ፊት በቃ ሊባል ሲገባ ዝም መባሉ ህግ ለእሱ እንደማይሰራ በእብሪት ያሰኘውን መናገር መቻሉ በቃህ ሊባል ይገባል እንላለን፡፡ ህግ በሌለበት ሃገር የማፍያ ሥርዓት የሚያራምዱ ህገ ወጥ ወንጀለኞች ይፈለፈላሉ፣ የህዝቡን ሠላምና ጸጥታ ማስከበርና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑ ካልተረጋገጠ ሃገሪቱ  በዘር የተገነባ የጦር አበጋዞች መንግስት ሥር ዳግም ትወድቃለች እንላለን፡፡ በትግራይ ክልል የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር አውሮፕላኖች፣ ታንኮች፣ የጦር ግምጃ ቤት ክምችት ወያኔን ለእብሪት ስራው ዳርጎታል በአፋጣኝ ወደነበረበት ቦታ መመለስ አለበት ፈርቶ ዝም ማለት ውሎ አድሮ ያስከፍላል፡፡

የህወሓትና የኦነግ የኢኮኖሚ አሻጥርን በህዝባዊ የራስ መተማመን (Selfe Reliance) ፖሊስ እንመክት

የዶክተር አብይ መንግሥት አዲስ ፊሲካል ፖሊሲ፤(Fiscal Policy) በመንደፍ የኢትዩጵያ መንግስት በግብርና ታክስ ልዩ ልዩ አሻጥሮች ያልተሰበሰበ ግብርን በልዩ ልዩ ገቢዎች ማጠናከር ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን የመቀነስ ፖሊሲን ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ተመጣጣኝ እንዲሆን እርምጃ መውስድ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ መንግስት የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን ማጠናከር እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን መቀነስ አስፈላጊ እርምጃ መውስድ ይኖርበታል፡፡  የህወኃት/ኢህአዴግ  የጦር አበጋዞች መንግሥትና በመላ ሃገሪቱ ሽብር ስፖንስር በማድረግ ህገወጥ ገንዘብና መሣሪያ በማሰራጨት ህዝቡን ሰላም በማሳጣት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሽመደመድ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ የወያኔን ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይል የኢኮኖሚ አቅም ድባቅ ለመምታት  የገንዘብ ገቢያቸውን  ምንጮች ማድረቅ፣ የመሣሪያ ስርጭታቸውን መቆጣጠር በተከታታይ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡  የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤ የግብርና ታክስ ስርዓት ገቢ እያሽቆለቆለ መሄድ አንዱ አሻጥር መሆኑን በመረዳት መንግሥት ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮችን መፈለግና የመንግሥት ወጪዎችን በመቀነስ ይሄን የኢኮኖሚ አሻጥር መግታት ይችላል እንላለን፡፡

  • የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በ2009 ዓ.ም 50 ቢሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ግብር ጉድለት ነበረበት፡፡
  • የገቢዎች ሚኒስቴር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ2010ዓ/ም 213 ቢሊዮን ብር የታክስ ገቢ እንደሚያሰባስብ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹መብቴን እጠይቃለሁ፣ ግዴታን እወጣለሁ ››
  • የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 10 ቢሊዮን ብር በአንደኛው ሩብ ዓመት መሰብስብ አልቻለም፡፡ የ2011 ዓ/ም መጀመሪያው ሩብ አመት ሪፖርት፣ በ2010ዓ/ም በጀት አመት የፀደቀው 346.9 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 241.94 ቢሊዮን ብር ገቢ ከታክስና ሎሎች ገቢዎች በመሰብስብ ለመሸፈን የታቀደ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን  ከአገር ውስጥ ገቢ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲሰበሰብ የታቀደው ገቢ 28.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን አፈጻጸሙ 25.62 ቢሊዮን ብር በመሰብስብ በእቅድና በክንውኑ መካከል የ3.2 ቢሊዮን ብር ልዮነት ታይቶል፡፡ እንዲሁም ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይ  መሰብሰብ አልተቻለም፡፡  በአጠቃላይ ከአገር ውስጥ ገቢ (3.2) ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ6.7 ከታቀደው የታክስ ገቢ ውስጥ 10 ቢሊዮን ብር መሰብስብ አልተቻለም፡፡ በመጪዎች ሩብ ዓመት የታክስ ገቢ መሰብስብና እንዳይቀንስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ፡፡
  • ህገወጥ የድንበርና የኮንትሮባንድ ንግድን፣ የምንዛሪ፣ የጥሬ ገንዘብና፣ የጦር መሣሪያ ዝውውርን መግታት ይኖርብናል፡፡
  • በየከተሞቹ ያሉ የህንፃ ግንባታዎች ሥራ መቀዛቀዝና የስራ አጥነት ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት በመሆኑ አዲስ የሥራ ፈጠራ ፕሮግራም መንደፍ ያስፈልጋል፡፡
  • የውጭ ንግድ ገቢ  እንዲጨምር ማድረግና የገቢ ንግድ ወጪ እንዲቀንስ ማድረግ  ያስፈልጋል፡፡

መንግሥት በራስ የመተማመን (Selfe Reliance) ፖሊሲ መቅረስ ይኖርበታል

{1} የሼህ መሃመድ አላሙዲን ሜድሮክና የህወሓት ኢዛና የወርቅ ማዕድን አውጭ ኩባንያዎች ከብሄራዊ ባንክ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ስውር መመሪያና በቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አቶ ሶፍያን አህመድ ወርቅ በህገወጥ መንገድ በመሸጥ የወንጀል ተግባር ላይ በመገኘታቸው   የወርቁን ማዕድን በመውረስ አዲሱ መንግስት እስከ 500 ሚሊዩን ዶላር በአመት የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላል እንላለን፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥሩን መንግሥት በዚህ መሰል እርምጃ መከላከል ይቻላል እንላለን፡፡

{2} ኦዴፓ/ ኢህአዴግ መንግሥት በራስ መተማመን (Selfe Reliance) አዲስ ፊሲካል ፖሊሲ፤ በመንደፍ የፌዴራልና የክልል  ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶችን የህዝብ ኃብትና ንብረት በማድረግ ገቢውን በትንሹ ከአምስት እስከ አስር ቢሊዮን ብር ገቢ በአመት መሰብሰብ ይችላል እንላለን፡፡ የህወሓት፣ብአዴን፣ ኦህደድ፣ ደኢህዴን የፖለቲካ ድርጅቶችና የንግድ ድርጅቶች የኢፈርት፣ ጥረት፣ ዲንሾና ወንዶ የከተማ ቤቶች ቅርምት፣ መንግሥት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶችን የህዝብ ኃብትና ንብረት በማስመለስና በአለው የቤት ገብያ ዋጋ ቢያከራይ  ብዙ ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ይችላል፡፡ ‹‹የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከታኅሳስ ወር መጀመርያ ጀምሮ በ6,635 የንግድ ቤቶቹ ላይ የኪራይ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡›› የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ‹‹… የሚያስተዳድራቸው ቤቶች ላይ የክፍያ ተመን ማስተካከያ ሳያደርግ ለበርካታ ዓመታት በመዝለቁ፣ የኪራይ ዋጋው ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ሆኖ ቆይቷል ሲል አስረድቷል፡፡ የክፍያ ዋጋውም ከግሉ ዘርፍ ጋር ከፍተኛ ልዩነት ያለው በመሆኑ የንግድ ውድድሩ እንዲዛባ አድርጓል በማለት የሚገልጸው ኮርፖሬሽኑ፣ የአሁኑን ጭማሪ በመቶኛ ማስላትም አግባብ ካለመሆኑም በላይ አሁንም ቢሆን ከግሉ ዘርፍ ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው ብሏል፡፡›› የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ‹‹… የንግድ ቤቶችና ድርጅቶች የክፍያ ተመን ለማሻሻል ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ጥናት ሲካሄድ ነበር ብሏል፡፡ የጥናቱ መነሻ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው ሪፎርም በዜጎች መካከል የተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር መፈለጉ ነው ሲልም አክሏል፡፡ በኮርፖሬሽኑ የንግድ ቤቶች መካከል የተለያየ የክፍያ ተመን እየተተገበረ በመሆኑ፣ በደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎች ለመፍታት ባልተመጣጠነና ገበያውን ባላማከለ የኮርፖሬሽኑ ተመን ምክንያት ያላግባብ በአቋራጭ የበለፀጉ ዜጎች በመፈጠራቸውና ለችግሩ ፍትሐዊ ምላሽ መስጠት አስፈልጓል ብሏል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች የክፍያ ተመን አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት የተለያዩ ሕገወጥነት ያላቸው ክስተቶች መፈጠራቸው በተለይም የሦስተኛ ወገን የአከራይ ተከራይና ቁልፍ ሽያጭ ለማስቀረት፣ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ስለሆነ ለጥገና፣ እንዲሁም አዳዲስ ሕንፃዎችን ለመገንባት ከዚህ የተሻለ አማራጭ ወቅት የለም ብሏል፡፡ ኮርፖሬሽኑ እንደሚለው የሚያስተዳድራቸው ቤቶች የክፍያ ተመን ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ከግሉ ዘርፍ አንፃር ሲታይ ደግሞ አሁንም ከፍተኛ ልዩነት አለው፡፡ ለአብነት ኮርፖሬሽኑ እንደገለጸው ከ6,635 የንግድ ቤቶች ውስጥ 279 ያህሉ በካሬ ሜትር ከአንድ ብር በታች እንደሚከራዩ፣ 2,057 የሚሆኑት የንግድ ቤቶች ደግሞ በካሬ ሜትር ከአሥር ብር በታች እየተከራዩ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲሱ የኪራይ ጭማሪ መሠረት በካሬ ሜትር እያሰላ ማስከፈል የሚጀምር ሲሆን፣ በካሬ ሜትር እስከ 500 ብር መጠየቁ ብዙዎችን አስቆጥቷል፡፡ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ በማድረግ የረጅም ጊዜ ደንበኞችን ማመሰቃቀል፣ ከበስተጀርባው የተደበቀ ሴራ አለው ሲሉ ተከራዮች ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ግን አሁን ካለው የገበያ ዋጋ አንፃር እንዲህ ያለ ብሶት ማቅረብ ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡ ጥናቱ ይፋ በተደረገበት የካፒታል ሆቴል ስብሰባ ወቅት አንዳችም ተቃውሞ ሳይቀርብ ስምምነት ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል፡፡››

{3}  የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት፣ የቀድሞው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ በደርግ መንግስት በአዋጅ የተወረሱ ቤቶችን እንዲያስተዳድርና አዳዲስ ቤቶችን እንዲገነባ የተቆቆቀመ ድርጅት ነበር፡፡ከ1983 ዓ/ም ወዲህ አዳዲስ ቤቶች እንዳይገነባ ፣ ያሉትን ቤቶች ብቻ እንዲያስተዳድር ተወስኖበት ነበር፡፡ ከ26 ዓመታት በሆላ ደግሞ፣በየካቲት ወር 2009 ዓ/ም እንደ አዲስ በድጋሚ የተቆቆመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ሲሆን፣ በማስተር ፕላኑ ዞን 3 እና 4 ውስጥ እስከ 10 ፎቅ የሆኑ በአጠቃላይ 16  ሽህ  ቤቶችን ለመገንባት እቅድ አውጥቶል፡፡ ቤቶቹ ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞችና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በኪራይ ለማስተላለፍ ነው፡፡ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደማንኛውም ዜጋ በ10/ 90፣ በ20/ 80 እና በ40/60 ቤቶች ተደራጅተው ቤት ሊገነቡ ሲገባ በህዝብ ገንዘብ በግብር ከፋዩ ደም የኪራይ ቤቶች ሊያገኙ አይገባም፡፡ ከ37 ሽህ ህዝብ በላይ የቤቶች መስሪያ የቁጠባ ሂሳቡን ሲዘጋ የህዝብ የቁጠባ ባህል ተስፋ በመቁረጥ አብሮ እንደቀበራችሁት የሚረዳ ህሊና ቢኖራችሁ ዛሬ ቆጥቦ ቤት የሚሠራውን ወገን በመርዳት 33 ቢሊዮን ብር ግንባታችሁን፣ ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ለሠራተኞች በየትኛው መልካም አስተዳደር ስነምግባራቸው፣ የሞራል ብቃታቸውና፣ ስብዕናቸው ነው በግብር ከፋዩ ገንዘብ ቤቶች የሚገነቡላቸው ይሄ አሠራር በመንግሥት በጀት፣ ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ሠራተኞች የቤት ግንባታ ማድረግ የጥቅም ግጭት፣ መጠቃቀምና፣ የአድልኦ አስራርን በሃገሪቱ ያሰፍናል፡፡ መንግሥት ቤት ለሌላቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎቹን ቤቶች ሠርቶ ሲያከራይ እንጂ መስራት ለሚችሉና ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ሲደጉም ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅ እንላለን፡፡ የፓርላማ አባላቶች ከመንግሥት ኪራይ ቤቶች ተሠጥቶቸው ይኖራሉ፡፡ ለመከላከያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖች በሲግናል ካንፕ፣ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት አካባቢ፣ገነት ሆቴል ምርጥ ኮንዶሚንየም ቤቶች ተሠርተው ለወያኔ ጀነራል  መኮንኖች ተሠጥቶል፣ ብዙዎቹ መሬት በነፃ ተሰጥቶቸው ቤት ሠርተው ያከራያሉ፡፡ ለደህንነት ሠራተኞች ከመንግሥት ኪራይ ቤቶች ተሠጥቶቸው ይኖራሉ፣ብዙዎቹ መሬት በነፃ ተሰጥቶቸው ቤት ሠርተው ያከራያሉ፡፡ ከመንግስት ቤት ተከራይተው ቤት ሠርተው የሚያከራዩትን ወያኔ ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ቪላ ቤቶች አስለቅቆ በገበያ ዋጋ ማከራየት የመንግሥት ገቢን ይጨምራል እንላለን፡፡

{4}  በፊዴራል ደረጃ ካሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል 77 ቢሮዎች፣ የራሳቸው ቢሮዎች/ህንፃ የሌላቸው ስለሆነ የግለሰብ ህንፃን እንደ ቢሮዎች ተከራይተው 380 ሚሊዩን ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡ አከራዬቹ የህወኃት/ ኢህአዴግ ሹማምንቶችና የጦር መኮንኖች እንደሆኑ መረጃውን የምታውቁ በማጋለጥ መተባብ ይኖርባችሆል፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት ከሹማምንጹ በአስለቀቃቸው ቪላ ቤቶችና መኖሪያ ቤቶች የራሱን ቢሮዎች በማዘዋወር በወር 31.6 ሚሊዮን ብር በዓመት  380 ሚሊዮን ብር የመንግሥት ወጪን መቀነስ ይችላል እንላለን፡፡ በኢኮኖሚ በራስ መተማመን  እንዲህ ነው እንላለን፡፡

{5} ዲያስፖራው ወገናችን ቃል የገባውን እንዲፈፅም ቅስቀሳውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡

ምንጭ፡-

1- ብርሃኑ ድንቄ አልቦ ዘመድ መጽሃፍ የተወሰደ፡፡

2-ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ‹‹ቤቶች ኮርፖሬሽን ባደረገው የንግድ ቤቶች የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ደንበኞች ቅሬታ አቀረቡ›› 23 December 2018

3- ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ‹‹ለቀበሌ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊዘጋጅ ነው ››16 December 2018

4- ሪፖርተር ጋዜጣ፣ በኢንሳ ሶፍትዌር ምክንያት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ቀን ተራዘመ 11 November 2018

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

‹‹ ዛሬን በነገ ዓይን›› ወይስ ‹‹ ነገን በዛሬ ዓይን ››ማየት!!!  

ሚሊዮን ዘአማኑኤል

  <<ሕይወት ማለት መብላትና መጠጣት፣ አዳዲስ ልብስ እያፈራረቁ መልበስ፣ ከባንክ ገንዘብ ማጠራቀም፣ አዲስ ‹‹ሞዴል›› መኪና ምንዳት፣… ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ በቀላሉ መንገድ ሊገኝ እንደሚችል አይተናል፡፡ ስብአዊ ክብር ግን በገንዘብ አይገዛም፡፡ ሐሪሶት (culture) የሌለው ሰብአዊ ክብር ምን እነደሆነ ማወቅ አይቻልም፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያጋጠመው ዋና ፕሮብሌም ነው፡፡>> ብርሃኑ ድንቄ

 ዶክተር ደብረፂዬንና ዳውድ ኢብሳ የለውጥ ህግ ‹‹ነገን በዛሬ ዓይን›› በማየት ጸረ ዴሞክራሲ የወያኔን አንባገነን፣ የጦር አበጋዞች መንግሥትን ለማምጣት የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ/አዴፓ/የደቡብ፣ጋምቤላ/ ሱማሌ፣ አፋር/ ሀረሪ/ ወዘተ ዴሞክራሲ ኃይል ይዘው ‹‹ዛሬን በነገ ዓይን›› በማየት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ወጣት የለውጥ ኃይልን በፍቅር አገር በጋራ መገንባት ነው፡፡

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ በዘራቸው ሳይሆን በሥራቸው የመለካት ባህል እናዳብር፣ ጥሩ ሲሰሩ በማመስገንና መጥፎ ሲሰሩ ቀሬታቸንን በመግለጽ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባህል ማዳበር አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡  

  ፊሲካል ፖሊሲ፤(Fiscal Policy) የኢትዩጵያ መንግስት የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሳያል፡፡ የመንግስትና የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን በአጠቃላይ የፊስካል ፖሊሲ መንደፍ አስፈለጊ ነው እንላለን፡፡ 

{1} በፋይናንሻል ኢንቲግሪቲ ድርጅት፣ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ  ከዓለም 180 ሃገራት 107ኛ ደረጃ፣ እንዲሁም ከአፍሪካ ሃገራት 20ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሙስና ከመቶ 35 በመቶ ውጤት በማግኘት ወድቃለች፡፡ በሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ የተጀመረው የሙስና እንቅስቃሴና የታሰሩት ግለሰቦችና የተወረሰው ንብረት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለህዝብ በየወሩ ሪፖርት ጠቅላይ ሚንስትሩ ማድረግና ለህዝብ የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት፡፡ የፀረ ሙስና ባህላችሁ ያዝ ለቀቅ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ነው፡፡

{2} የጠቅላይ ኦዲተር ፅህፈት ቤት በተደጋጋሚ ለፓርላማ ያቀረቡት የኦዲት ሪፖርት ድጋፍ ተሰጥቶት በፍርድ ቤት ፍትህ እንዲሰጥና የህግ ተፈፃሚነት ተግባራዊ ማድረግ፡፡ የጸረ- ሙስናውን ትግል በነጻነት እንዲመሩና በሃገሪቱ ውስጥ የተስፋፋውን ሙስና፣ ኮንትሮባንድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገወጥ ግለሰቦችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት መስጠት፣ ከህግ በላይ ማንም ሰው መሆን እንደማይችል በተግባር መገለፅ አለበት፡፡   

{3} ሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ ከነሰንኮፉ ነቅሎ መጣልና የአይነኬ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ንብረታቸውና ሃብታቸው በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማስመዝገብና የሃብትና የንብረት ምንጫቸው ለህዝብ ማሳወቅ ግድ ይላል፡፡   

{4} የከተማና የገጠር የመሬት ቅርምት፣ የእርሻ መሬት፣ የሪል ስቴት መሬት፣ የአበባ መሬት፣ ወዘተ ህገወጥ የሙስና ተግባር፣ ህዝብ የተሳተፈበት የማጋለጥ ሥራ በመገናኛ ብዙሃን ሬዲዮ፣ቴሌቪዝን፣ ጋዜጣ ፣ ኢንተርኔት ይፋ ማድረግ

{5} በፕራይቬታይዜሽን የተሸጡ የህዝብ ሃብቶችና ንብረቶች የእርሻ ቦታዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆቶሎች፣ ወዘተ በጸረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ እንዲካሄድባቸው ማድረግ፣

{6} የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃብትና ንብርት የሆኑ ድርጅቶች የህወሓት ኢፈርት፣ የበአዴን ጥረት፣ የኦህዴድ ዲንሾ እንዲሁም የደህዴን ወንዶ የንግድ ድርጅቶች ፋብሪካዎች፣እርሻዎች፣ የማዕድን ሓብቶች ወርቅ፣ ብር ፣ታንታለም፣ እብነበረድ፣ሲሚንቶ ፣ የአገልግሎት ሰጪ የንግድ ድርጅቶች፣ የመድሃኒት ፋብሪካ፣ የማዳበሪያ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ወዘተ የፓርቲ የንግድ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍና ተቆማት  ያለው የሙስና ተግባር ሥራዎች ተጋልጠው እንዲወጡ ማድረግ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ንብረት የሆኑት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ተወርሰው ፣ ባንኮቹ ለህዝብ በአክሲዮን ተሸጠው የህዝብ ሃብት ማድገር፣

{7} የፋይናንሻል ዘርፍና ተቆማት በመንግሥት ባንኮችና የግል ባንኮች፣ በማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ያለው የሙስና ተግባር ብድር በመስጠት፣ በመሰብሰብ፣ በውጭ ምንዛሪ፣ ለመንግሥት፣ ለክልሎች፣ ለግለሰቦች በአድሎ የተደረጉ ሥራዎች ተጋልጠው እንዲወጡ ማድረግ፤ የህወሓ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ንብረት የሆኑት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማት 50 ቢሊዮን ብር ንብረት ተወርሰው ፣ ባንኮቹ ለህዝብ በአክሲዮን እንዲሸጡ ማድገር፣

{8} የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ቤት እያከራዩ የመንግሥት ቤት ውስጥ የሚኖሩ በአስቸኮይ እንዲወጡ፣ እንዲሁም ቤት እያከራዩ በቀበሌና በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች ተጣርቶ እንዲለቁ ማድረግ፣

{9} የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ከአንድ መጠቀሚያ የመንግሥት መኪና በስተቀር ሌሎቹን ማስመለስ

{10} በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ሑለት ሦስት የመንግሥት ቦታ የወሰዱ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንት፣ የጦር መኮንኖች፣ ካድሬዎች ለመሬት ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ፡፡ ሜድሮክ አጥሮ የያዛቸው 11 ቦታዎች ካርታ ማምከን!!! በ‹‹ልማት ተነሺ›› በማለት የሚነሱ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ይቁም፡፡ በግፍ የተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው ካሳና ቤት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡ በሙስና ሁለት ሦስት የኮንዶሚኒየም ቤቶች የተሰጣቸው ግለሰቦች እንዲመልሱና ተጀምሮ የነበረው የኮንዶሚኒየም ቆጠራ፣ የህዝብ ሃብት እንዲጠናከር ማድረግ፡፡

የወያኔ የመንግሥት የገማ መሥሪያ ቤቶች አሠራርንና አደረጃጀትን በመቀየር የመንግሥትን ወጪ መቀነስ ያስፈልጋል

 {1} በፊዴራል ደረጃ ካሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል 77 ቢሮዎች፣ የራሳቸው ቢሮዎች/ህንፃ የሌላቸው ስለሆነ የግለሰብ ህንፃን እንደ ቢሮዎች ተከራይተው 380 ሚሊዩን ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡ አከራዬቹ የወያኔ ሹማምንቶችና የጦር ጀነራሎች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ላይ እርምጃ አለመውሰድ የህወሓትና ኦነግ ፀረ ዴሞክራሲው  ኃይል ለውጡን እንዲቦረቡር መፍቀድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ የኢኮኖሚ የገንዘብ ምንጫቸውን ማድረቅ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡  የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት በ1983 አ.ም ፤ በከተማ ልማት፤ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፤ የመንግስት ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ (የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ) በመቆጣጠር በአዲስ አበባና በሌሎች አገሪቱ ክልሎች የሚገኙ በድምሩ 17,549 ቤቶች ማስተዳደር ጀመረ፡፡ ለሚኒስትሮች፣ ጀነራሎች፣ የደህንነት ሹሞች፣ ዲፕሎማቶች የመንግሥት ቤት ተከራይተው ቤት ሰርተው የሚያከራዩ የነቀዙ ሹመኞች በሙስና ያገኙትን የግብር ከፋዩን የደሃ ዜጋ ቤት ማስረከብ  በአዲሱ ለውጥ ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ ከነዚህም ቤቶች ውስጥ በመግባት በፊዴራል ደረጃ ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች  ቢሮዎች በማድረግ፣ለቢሮዎች ኪራይ የሚወጣው 380 ሚሊዩን ብር በዓመት ክፍያን ማዳን ይቻላል እንላለን፡፡ የህወኃት ኢህአዴግ ሹማምንት በሙስና ለቤት መሥሪያ የተሠጠ መሬትና ቤት በጥናት ተደግፎ ለህዝብ ይቅረብ፣ ከዚህ በኃላም ለሹማምንቶችና ካድሬዎች የሚሰጥ ቤሳ ቤስቲን መሬት መኖር የለበትም!!! መንግሥት የራሱን ቢሮዎች ሳይሰራ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ተከራይቶ መኖር ለከፍተኛ ወጪና በግብር ከፋዩ ህዝብ ኃብት መቀለድ በመሆኑ መቆም አለበት፡፡

 {2} በኢፈዴሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲና የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ፣ በየካቲት ወር 2009 ዓ/ም እንደ አዲስ በድጋሚ የተቆቆመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ሲሆን፣ በማስተር ፕላኑ ዞን 3 እና 4 ውስጥ እስከ 10 ፎቅ የሆኑ በአጠቃላይ 16  ሽህ  ቤቶችን ለመገንባት እቅድ አውጥቶል፡፡ ቤቶቹ ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞችና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በኪራይ ለማስተላለፍ ነው፡፡  በመንግሥት በጀት፣ ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ሠራተኞች የቤት ግንባታ ማድረግ የጥቅም ግጭት፣ መጠቃቀምና፣ የአድልኦ አስራርን በሃገሪቱ ያሰፍናል፡፡ የ10/90 እና 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ከ20 እሰከ 30 ቢሊዮን ብር ቁጠባ ሂሳብ አስቀምተው ሰባት አመት ቤት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡መንግሥት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ለሹማምንቶቹ 33 ቢሊዮን ብር  መመደቡ ሌብነት ነው እንላለን፡፡ የንግድ ባንክ የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት፣ በግልፀነትና ታማኝነት ካልተሠራ ገንዘባችሁ ይዘረፋል ተጠንቀቁ!!!  

{3} የ40/60 የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም 37000 (ሠላሳ ሰባት ሽህ) ተመዝጋቢዎች 7 እስከ 10 ዓመታት ጠብቀው፣ተስፋ በመቁረጥ ውላቸውን አቆርጠዋል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2005 ዓ/ም ይፋ ባደረገው አራት የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች የ10/90 እና 20/80  የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሚሊየን ነዋሪዎች ተመዝግበው ባንክ እየከፈሉ 7 አመታት አስቆጥረዋል፡፡ በ1996 ዓ/ም በተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታ እስከ 2010ዓ/ም ድረስ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ 175 ሽህ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ የ40/60 ቤቶች ጨምሮ ከ132 ሽህ በላይ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ የ40/60 የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም 164000 (መቶ ስልሳ አራት ሽህ ሰዎች ተመዝግበው 37000 (ሠላሳ ሰባት ሽህ) ከተመዝጋቢዎቹ 23 በመቶ፣ ዜጎች ተስፋ በመቁረጥ ውላቸውን አቆርጠዋል፣ በቀጣይነት ለ40000 (አርባ ሽህ ሰዎች)ቤት ለመስጠት እቅድ እንዳለ ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ/ም በቴሌቪዥን ገልፀዋል፡፡ ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሦስትና አራት አመት ሠርተው እናስረክባለን ብለው የህዝብ ገንዘብ ሰብስበው በተግባር ቤቶቹን ሠርተው ባለማስረከባቸው ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡ በሃገሪቱ ህዝብ የገንዘብ ቁጠባ ባህልን ያጠፋት ሁለቱ ድርጅቶች ሥራቸውን በአግባቡ ስላልተወጡ ለህግ መቅረብና በሌሎች ብቃት ያላቸው ሙያተኞች መተካት ይኖርባቸዋል፡፡ ቤት ሰሪው ህብረተሰብም ለ7 ዓመታት በቤት ኪራይ እየተሰቃየ፣ ለተጨማሪ የቤት መሥሪያ ወጪ የዋጋ ግሽበት ተጠያቂ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ባንኮች በየአመቱ ከ10 እስከ 14 ቢሊዮን ብር አተረፍን እያሉ የሚተርኩት የደሃውን ህብረተሰብ ተቀማጭ ገንዘብ እያበደሩ ባገኙት ትርፍ መሆኑ ይታወቃል ስለዚህ በህግ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ካገኙት ትርፍ የእነዚህን ደሃ ህብረተሰብ ቤቶች መስሪያ የዋጋ ግሽበት ተጨማሪ መክፈል ይገባቸዋል፡፡ የዲያስፖራ ወገኖች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያዘጋጀውን‹የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት›በህግ ተዋውላችሁ፣ መብታችሁን አስከብራችሁ በሃገራችሁ ውስጥ ቤት ሠርቶ የመኖር ነፃነታችሁን ማስጠበቅና ሃገራችሁን መርዳት ይጠበቅባችሆል፡፡ ዲያስፖራዉ ወገናችን ቤት ለመገንባት ብለው በተለያዩ ሪል  እስቴት ዲቨሎፕርስ ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል ከጃክሮስ ኢትዮጵያ እስከ ካንትሪ ክለብ ከውል ውጪ የአምስት መቶ ሽህ ብር ጭማሪ እየተደረገባቸው ቤታቸውን አጥተዋል፣ በአክስስ ሪል ስቴት ገንዘባቸውን ያጡ ዜጎች ሊመለስላቸው ይገባል እንላለን፡፡

{4} የመንግሥት ወጪዎችን ለመቀነስ አንደኛው የቅንጦት መኪኖች ቢኤይት መኪኖችን ለመንግሥት ትንሽ አስቀርቶ ለግሉ ዘርፍ በጨረታ መሸጥ፣ የመንግሥት የነዳጅ ወጪን መቀነስ

{5} የመንግሥት ወጪዎችን ለመቀነስ አንደኛው የቅንጦት መኪኖች ቢኤይት፣ ሃመር ወዘተ ልዩ ልዬ  መኪኖችን፣ ሽቶ፣ ሲጋራ፣ መጠጦች በአጠቃላ ለቅንጦት እቃዎች  ኢኮኖሚው እስኪያንስራራ ድረስ ሃገር ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግና የውጭ ምንዛሪ ማገድ ያስፈልጋል፡፡

{6} የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ በአስሩ ክፍለ ከተሞች በወረዳና ቀበሌዎች የተሰገሰጉ የወያኔ ነጭ ለባሽ ሰላዬችን በለውጡ ኃይል እስካሁን ባለመተካትዎ የፀረ ዴሞክራሲው ኃይል ህዝቡ አዲሱን ለውጥ እንዲያማርር፣ የቤት ኪራይ በየጊዜው በመጨመር ደሃውን ህዝቡ መበዝበዝ፣ የምርትና ሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ጭማሪ ማሰመረር፣ ተንጎተተ ቢሮክራሲ አሰራር መቀጠል፣ የግብርና ታክስ አሰባሰብ ዝግምተናነትና ሠራተኞቹ ከቢሮቸው አለመገኘት፣ ሥራ ተሠፍሮ ያልተሠጣቸው በፖለቲካ ካድሬነትና ሰላይነት የተሰገሰጉ ደም መጣጮችን በአፋጣኝ መተካት ያስፈልጋል እንላለን፡፡

{7} የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም የቴሌቨዝን ፣ ሬዲዬና ኤፍ ኤም ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ሥራን አበክራችሁ ልትሰሩበት ይገባል እንላለን፡፡

{8} የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣የአዲስ አበባ ህብረ ብሄር ወጣቶች ማህበር ከማንም የፖለቲካ ድርጅትጣልቃ ገብነት እንዲመሠረትና እንዲጠናከር የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው እንላለን፡፡

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣

የከተማ መሬት ቅርምት መግታት፣ የሼህ መሃመድ አላሙዲን በአዲስ አበባ ከተማ አጥረው ያስቀመጡትን አስራ አንድ መሬቶች በደ ህዝብ የመሬት ባንክ ንብረትነት በማስመለሰቸው ህዝባዊ ድጋፋችንን ስንገልፆልዎ በቀጣይም የአዲስ አበባን ወጣቶች ከዘር፣ ኃይማኖት፣ ቀለም፣ ከጾታ ልዩነትን ሳይለያይ ለሰው ልጅ፣ ለስብአዊ ክብርና ጠንካራ የማይንሸራተት ባህል በፍቅር እንዲገነባ የታሪክ አደራ በእርሶ ላይ ወድቆል፣ ለህዝብ የገቡትን ቃል ኪዳን በተግባር በመግለጽ፣ ከህዝብ ጋር አብሮ በመስራት ምን አጠፋን ምን አለማን እያሉ ህዝቡን ዘወትር በማማከር ህዝባዊነትዎን በማሳየት ይቀጥሉበት እንላለን፡፡ ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በሚያስተዳድረው መዲና በመልሶ ማልማት  ፕሮግራም የሚፈናቀል አንድም ሰው እንደማይኖር አቆም በመያዛችሁ ህዝቡ ተረጋግቶ በህሊና ሰላም አግኝቶ ተመስገን ብሎል፡፡ ህዝብ ከ27 አመት ባርነት የ1 ቀን ነፃነት ብሎል ዳግም ወደ ባርነቱ ከሚገባ ሞቱን ይመርጣልና!!! 

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም 28 ሪል ስቴት ኩባንያዎች፣ በሙስናና ሌብነት በተደረገ የከተማ መሬት ቅርምት ተጠቃሚዎች ላይ እርምጃ መውስዱ ተገቢ ነው፡፡ ከ1996 ዓ/ም ጀምሮ በርካታ ሪል ስቴት ዘርፍ የመሬት ዘረፋ በከተማው ደሃ ህዝብ መሬትን በማፈናቀል  የተደረጉ ወንጀሎች ተጠያቂ ኩባንያዎች በህግ እንዲቀርቡ መደረግ ይኖርበታል፡፡ የሪል ስቴት ኩባንያዎቹ፣ ባለቤቶች፣ የመሬት ሊዝ የከፈሉበት ሰነድ፣ ቤት ገንብተው ያስተላለፉላቸው ግለሰቦች ዝርዝርና የተላለፈበት ዋጋ የያዙ ሰነዶችና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ከአስሩ ክፍለ ከተሞች የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ፅህፈት ቤቶች መረጃው ተጠናክሮ በማቅረብ ፌዴራል ፖሊስ፣ ለፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ በፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰረትባቸው ማድረግና የሌሎቹንም ሪል ስቴት ኩባንያዎች በአፋጣኝ ተከታትሎ መረጃ እንዳያጠፉ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡  ህዝቡ ከጎናችሁ መሆኑን እንገልፅላችሆለን፡፡  አስተዳደሩ የሚያወጣቸውን ማስታወቂያዎች ለዴሞክራሲ ለታገሉት ጋዜጦች ድጋፉን ያድርግላቸው፡፡  ከ2002 ዓ.ም. ለ160 ሪል ስቴት ኩባንያዎች ተመስርተው ሥራ ጀምረው ነበር፡፡ ሪል ስቴቶቹ  ከከተማ አስተዳደሩ መሬት ወስደው ባለማልማት፣ የወሰዱትን ቦታ ሳያለሙ ለሦስተኛ ወገን በመሸጥና በማስተላለፍ፣ በወሰዱት የግንባታ ፈቃድ መሠረት ሳይሆን በራሳቸው ፍላጎት በመገንባት፣ ህገወጥ ሥራ በመስራት ከወያኔ ሹማምንቶች ጋር በመመሳጠር ወንጀል ሲፈፅሙ ነበር፡፡ ምክትል ከንቲባ ታከለ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ሕጋዊነት ጉዳይ እንዲመረመር በማዘዛቸው ሊመሰገኑ ይገባል እንላለን፡፡

በሕገወጥነት የተጠረጠሩ 28 ትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ታገዱ፣ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሕገወጥነት የጠረጠራቸውን 28 ትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች አገደ፡፡..  የታገዱት የሪል ስቴት ኩባንያዎች ኖህ ሪል ስቴት፣ ሰንሻይን፣ አያት፣ ሳትኮን ኮንስትራክሽን፣ ሴንቸሪ 21 ኮንስትራክሽን፣ ሙለር፣ ሳንታ ማርያ፣ ዋይቲዋይ ኮንስትራክሽን፣ ኃይሌና ዓለም ሪል ስቴት፣ ሰዒድ መሐመድ፣ ማኅተባይ ሪል ስቴት፣ አደይ አበባ፣ ፍሰሐ ሴት፣ ናታን፣ ጌታቸው ወልዴ፣ ወልመስ ኮንስትራክሽን፣ ሐውስ ዊዝደም የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ዮሐንስ ካሳዬ፣ የማናት፣ ዛምራ ትሬዲንግ፣ ማክሮ፣ ሮማናት፣ ፀሐይ ሪል ስቴት፣ መክሊት ሪል ስቴት፣ ጎላጉል ሪል ስቴት፣ ካሩቱሪ ሪል ስቴት፣ ባታ ሪል ስቴትና ፈቃዱና ጓደኞቹ ሪል ስቴት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ የሪል ስቴት ኩባንያዎች የተጠረጠሩት በሕገወጥነት፣ በተለይም መሬት ያገኙበት መንገድ፣ ግንባታ የሚያካሂዱበት አግባብ፣ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ የሚያቀርቡት የአገልግሎት ጥያቄ ብዛትና ፍጥነት የአስተዳደሩን ጥርጣሬ ከፍ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡  ‹‹ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ የሚደረገው የስም ማዘዋወር ሩጫ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሀብት እንደ ማሸሽ ይቆጠራል፤›› በማለት የገለጹት ኃላፊው፣ ‹‹የታገዱት የሪል ስቴት ኩባንያዎች ሰሞኑን በተለያዩ ወንጀሎች ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል የሚል ጥርጣሬ በሰፊው ተፈጥሯል፤›› በማለት፣ አስተዳደሩ የወሰደውን የጥርጣሬ ዕርምጃ መነሻ ምክንያት አብራርተዋል፡፡ የተቋቋመው ኮሚቴ ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ጋር በቅንጅት ጥናት ካካሄደ በኋላ ሕጋዊ ሆነው ለሚገኙት አገልግሎት መስጠትን የሚጀምር መሆኑን፣  ችግር እንዳለባቸው ማረጋገጫ በሚቀርብባቸው ላይ ደግሞ የማስተካከያ ዕርምጃ ይወስዳል ተብሏል፡፡

በሕገወጥ መንገድ የተያዙ 500 ቤቶች በዕጣ ሊከፋፈሉ ነው፣ ‹‹ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ባደረገው ጥናት፣ በሕገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 500 ቤቶችን በማግኘቱ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በዕጣ ሊያከፋፍል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት፣ ሰናይት ዳምጤ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት፣ ከከተማ እስከ ወረዳ በተዘረጋ ጥናትና ክትትል እስካሁን 500 የጋራ መኖሪያ ክፍት ቤቶች፣ በሕገወጥ መንገድ የተያዙና ውል የሌላው ቤቶች ተገኝተዋል፡፡ ቢሮው ባለፉት ወራት በሕገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን፣ የኮንዶሚኒየም መኖሪያና ንግድ ቤቶችን ኦዲት ማድረጉንም የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ በተለይ የቀበሌ ቤት ሆነው የፈረሱ፣ የጠፉ፣ የኪራይ ተመን የሌላቸው፣ ኪራይ የማይከፈልባቸው፣ ውል የሌላቸው፣ ከሕጋዊ ይዞታ ጋር የተቀላቀሉ፣ ተቀጥለው የተሠሩ፣ ተሸንሽነው የተከራዩ፣ ከግለሰብ ይዞታ ጋር ተቀላቅለው ተመላሽ የተደረጉና መረጃና ባለቤት የሌላቸው ቤቶች እንዳሉ ጥቆማ ስለደረሳቸው፣ በሦስት ከፍለው እየሠሩ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡  ሥራውን ከራሳቸው ቢሮ በመጀመር መረጃ የማጣራት ሥራ ማከናወናቸውንና በርካታ የቀበሌና የኮንዶሚኒየም ቤት መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም ሥራውን ወደ ክፍላተ ከተሞች በማውረድ መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑን፣ ለዚህም ኅብረተሰቡ በየክፍላተ ከተሞቹ ለዚሁ ሥራ በተከፈቱ ቢሮዎች ጥቆማ እንዲሰጥ ኃላፊዋ ጥሪ አድርገዋል፡፡  ጠፍተዋል የተባሉት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ያልተገነቡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ 550 መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት እነዚህና የተጀመሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በፍጥነት ተገንብተው ለተመዝጋቢዎች እንደሚተላለፉ አስታውቀው፣ ተመዝጋቢዎች ቁጠባቸውን ያለማቋረጥ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡››  

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የከተማዋን የመጸዳጃ ቤት ችግር ቅረፉለት!!!

 “በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም” 19 ኖቬምበር 2018 ዛሬ ታስቦ በዋለው የዓለም የመጸዳጃ ቤት ቀን በወጣ አንድ ዘገባ በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መሠረታዊ መጸዳጃ ቤት በቤቱ እንደማያገኝ ተገለጸ። ዘገባውን ያወጣው “ዎተር ኤይድ” የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው።  ለዜጎቿ መሠረታዊ የመጸዳጃ ቦታ ባለማቅረብ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገሮች ቀዳሚ ሆናለች። ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ከዓለም እጅግ የከፋ የመጸዳጃ ቤት አቅርቦት ችግር ያለባት አገር ሆና ተመዝግባ ነበር። ቻድ፣ ማዳጋስካርና ደቡብ ሱዳን 90 ከመቶ የሚሆነው ሕዝባቸው በቂ መጸዳጃ ቦታን አያገኝም። ጎረቤት ኤርትራ 83 በመቶ ሕዝቧ በመኖሪያ ቤት ውስጥ መጸዳጃ ቤት እንደማያገኝ ዎተር ኤይድ ያጠናቀረው ጥናታዊ ዘገባ ያስረዳል። ከሰሀራ በታች ብቻ 340 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝብ በቂና መሠረታዊ የመጸዳጃ አገልግሎትን አያገኝም። ይህም ለተቅማጥና ሌሎች ውሀ ወለድ በሽታዎች ያጋልጠዋል። የዓለም የመጸዳጃ ቀን ታስቦ በዋለበት በዛሬው ዕለት በወጣው በዚህ ዘገባ መሠረት በአህጉሪቱ ትምህርት ቤቶች በቂ መጸዳጃ ቤቶች ባለመኖራቸው 60 ከመቶ የሚሆኑ ሕጻናት ለችግር ይዳረጋሉ።

ኢትዮጵያ ከ157 አገሮች የጤና እና የትምህርት ሥርዓቶች ( በሰብዓዊ ካፒታል ምዘና ) በ135ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ካፒታል ምዘና ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ውጤት ከተሰጣቸው አገሮች ተርታ ተመድባለች። ባለፈው ሳምንት የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት በጋራ ባካሔዱት ስብሰባ ላይ ይፋ በተደረገው መመዘኛ ኢትዮጵያ 135ኛ ደረጃ ላይ ብትገኝም ለዘርፉ ትኩረት የሰጠች ተብላለች።

ሰው በዘሩ ሳይሆን በሥራው የሚለካበት የአዲሱ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች ባህል ሊሆን ይገባል!!!

የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች በእውቀት የፖለቲካ ሳይንስ፣የወታደራዊ ሣይንስ፣ የዲፖሎማሲና የደህንነት ሳይንስን በትምህርትን ይገነባሉ!  

የህወሓት/ ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶች በአክሲዬን ለህዝብ ይሸጡ!!!

ምንጭ፡-

1- ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ‹‹ቤቶች ኮርፖሬሽን ባደረገው የንግድ ቤቶች የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ደንበኞች ቅሬታ አቀረቡ›› 23 December 2018

2- ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ‹‹ለቀበሌ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊዘጋጅ ነው ››16 December 2018

3- በሕገወጥነት የተጠረጠሩ 28 ትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ታገዱ 19 December 2018

4- በሕገወጥ መንገድ የተያዙ 500 ቤቶች በዕጣ ሊከፋፈሉ ነው 26 September 2018

5- “በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም” 19 ኖቬምበር 2018

6- ኢትዮጵያ ከ157 አገሮች የጤና እና የትምህርት ሥርዓቶች ( በሰብዓዊ ካፒታል ምዘና ) በ135ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

Leave a Reply