
ህወሓት ከአማጺ ቡድንነት ተነስቶ ወታደራዊውን መንግሥት ከሥልጣን በማስወገድ ለአምስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ጉልህ ቦታን ይዞ ቆይቷል። ቡድኑ ለሁለት ዓመታት በቆየው ጦርነት ምክንያት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ ሕጋዊ ዕውቅናውን ተገፎ ቆይቷል። ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ወደ ፖለቲካው መድረክ የተመለሰው ህወሓት ሕጋዊ ዕውቅናው እንዲመለስለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አላገኝም። ይህ ውሳኔ የሚጸና ከሆነ ህወሓት ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?
Source: Link to the Post