የህወሓት ቡድን ከሃገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ተገለጸ፡፡…

የህወሓት ቡድን ከሃገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ተገለጸ፡፡…

የህወሓት ቡድን ከሃገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-24/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር የህወሓት ቡድን ከሃገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ገልጸዋል። አፈ ጉባኤው እንደገለጹት ቡድኑ ህገወጥ ድርጊቱን እንዲያቆም በምክር ቤቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግለትም ህገ-መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ከማድረግ ሊቆጠብ አልቻለም ነበር ብለዋል። ይህን ተከትሎም የህወሓት ምክር ቤት እንዲፈርስ ስራ አስፈጻሚው አካልም ዕውቅና እንዳይኖረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሰዋል። በክልሉም ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ምክር ቤቱ መወሰኑና ውሳኔው ህገ-መንግስቱን ለማስፈጸም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 359/95 መሰረት በማድረግ ነው ብለዋል። መንግስት ይህን ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የወሰደው እርምጃ የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ መሆኑንም ገልጸዋል። የህግ ማስከበር ዘመቻው በህገ- መንግስቱ መሰረት በብቃትና በውጤታማነት መፈጸሙንም ምክር ቤቱ ገምግሟል ብለዋል አፈ ጉባኤው። ምክር ቤቱ በቀጣይም በትግራይ ክልል የሚከናወኑ ተግባራት በህገ -መንግስቱ መሰረት መፈጸም አለመፈጸማቸውን እንደሚከታተል አስረድተዋል። በዚህ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በክልሉ ስላለው ሁኔታ በቀጣይ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባሉም ነው ያሉት። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply