የህወሓት ታጣቂዎች ጭናና ቆቦ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን ህዩማን ራይትስ ዋች አስታወቀ

የትግራይ ኃይሎች ከነሐሴ 25 እስከ ጳጉሜ 4 / 2013 ዓ.ም በነበሩት ቀናት ውስጥ በአማራ ክልል ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ ሁለት ከተሞች በትንሹ 49 ሲቪሎችን መግደላቸውን ህዩማን ራይትስ ዋች ዛሬ አስታውቋል።

የመብቶች ተሟጋቹ ቡድን ዛሬ ባወጣው ሪፖርቱ እነዚህ ግድያዎች የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ቢሮ፣ ወደ ሌሎችም አካባቢዎች በተስፋፋው የትግራይ ግጭት “በሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ይፈፀማሉ” ባላቸው የመብቶች ጥሰቶች ላይ “ዓለምአቀፍ አሠራርን የተከተለ ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ያመላክታሉ” ሲል አሳስቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply