የህወሓት አመራሮች  ዛሬም በቁጥጥር ስር ዋሉ። በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ አመራሮችም እርምጃ እንደተወሰደባቸው መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል። በዚሁ መሰረት እርምጃ…

የህወሓት አመራሮች ዛሬም በቁጥጥር ስር ዋሉ። በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ አመራሮችም እርምጃ እንደተወሰደባቸው መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል። በዚሁ መሰረት እርምጃ…

የህወሓት አመራሮች ዛሬም በቁጥጥር ስር ዋሉ። በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ አመራሮችም እርምጃ እንደተወሰደባቸው መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል። በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡- 1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበሩና አሁን የህወሓት ሎጂስቲክ ሃላፊ 2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበሩና በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ ህወሓትን የተቀላቀሉ 3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች 4ኛ – ሁለት መስመራዊ መኮንኖች 5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበሩና ከፖሊስ ከድተው ወደ ህወሓት የተቀላቀሉ ናቸው። በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰራዊቱ ማምሻውን ገልጿል። እነዚህም ፦ 1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩ 2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩ 3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበሩ 4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበሩ 5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበሩ 6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበሩ 7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ኢዜአ እንደዘገበው በተጨማሪም ሁለት ከሀገር መከላከያ ከድተው ህወሓትን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ ናቸው::

Source: Link to the Post

Leave a Reply