የህወሓት እና የፌደራል መንግስት ድርድር ተራዘመ። በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሊጀመር የነበረው ድርድር ቀኑ መራዘሙ ተነግሯል።የሮይተርስ ዜና ምንጭ የዲፕሎማሲ ም…

የህወሓት እና የፌደራል መንግስት ድርድር ተራዘመ።

በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሊጀመር የነበረው ድርድር ቀኑ መራዘሙ ተነግሯል።

የሮይተርስ ዜና ምንጭ የዲፕሎማሲ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ባወጣው ዘገባ ድርድሩ የተራዘመበት ምክንያት የሎጂስቲክስ ክፍተት ነው ተብሏል።

ስማቸው ያልተጠቀሱት ምንጮች እስካሁን ተለዋጭ ቀን እንዳልተቀመጠ ገልፀዋል።

ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ጊዜያት የቀሩትን ጦርነት ለመቋጨት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እንዲሁም በኡሁሩ ኬንያታ እና ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ መሪነት በደቡብ አፍሪካ እሁድ መስከረም 29 ቀን የሰላም ንግግሩ እንዲጀመር ቀጠሮ ተቀምጦ ነበር።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply