የህወሓት የሽብር ቡድን በኮምቦልቻ በቆየባቸው ጊዜያት ከ407 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን እንዳወደመበት የጉምሩክ ኮሚሽን ተናገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2…

የህወሓት የሽብር ቡድን በኮምቦልቻ በቆየባቸው ጊዜያት ከ407 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን እንዳወደመበት የጉምሩክ ኮሚሽን ተናገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኮሚሽኑ እንዳለው በቡድኑ የጥፋት በትር ካረፈባቸው መንግሥታዊ ተቋማት መካከል የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አንዱ ነው፡፡ ዘራፊው ቡድን በከተማዋ በቆየባቸው ቀናት ውስጥ የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ንብረቶችን ዘርፏል፣ ያልቻለውንም አውድሟቸዋል ተብሏል። በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የደረሰውን ውድመት በተመለከተ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ምክትል ኮሚሽነሮች እና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ቦታው ድረስ በመሔድ ምልከታ አድርገዋል መባሉ ተወርቷል። ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በከተማዋ ለሚገኙ ፋብሪካዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ እና ለሌሎችም ግዙፍ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ የወደሙ ንብረቶችን መልሶ በመተካት በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ይደረጋል ብለዋል፡፡ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የደረሰውን ውድመት እና ዝርፊያ ለማወቅ በተደረገው ጥናት መሰረት በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ የነበሩ 252.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ኮንቴነሮች ተዘርፈዋል፡፡ በጉምሩክ መጋዘን የነበሩ እና 94.7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ እቃዎች ወድመዋል ተብሏል። 46.6 ሚሊዮን የሚያወጡ የተያዙ እና የተወረሱ ተሽከርካሪዎች በአሸባሪው ቡድን ተዘርፈዋል፤ 13.1 ሚሊዮን የሚገመቱ ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ከባድ ውድመት እና ዝርፊያ ተፈጽሞባቸዋል ብሏል ኮሚሽኑ። አሸባሪው የህወሓት የሽብር ቡድን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቋሚና አላቂ ንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎች እና ገቢ እቃዎች ላይ ያደረሰው ጥፋት 407.7 ሚሊዮን ብር መገመቱም ተነግሯል ሲል የዘገበው ሸገር ኤፍ ኤም ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply