You are currently viewing የህወሓት የበላይነት በነገሰበት መከላከያ ውስጥ በኮማንዶነት ተመርቆ ያገለገለው፣ በመጨረሻም የለየለት ዘረኛ አካሄድን ባለመቀበሉ ከስራው የተባረረው እና በ2008 ዓ/ም ታስረው በጠንካራ ህዝባ…

የህወሓት የበላይነት በነገሰበት መከላከያ ውስጥ በኮማንዶነት ተመርቆ ያገለገለው፣ በመጨረሻም የለየለት ዘረኛ አካሄድን ባለመቀበሉ ከስራው የተባረረው እና በ2008 ዓ/ም ታስረው በጠንካራ ህዝባ…

የህወሓት የበላይነት በነገሰበት መከላከያ ውስጥ በኮማንዶነት ተመርቆ ያገለገለው፣ በመጨረሻም የለየለት ዘረኛ አካሄድን ባለመቀበሉ ከስራው የተባረረው እና በ2008 ዓ/ም ታስረው በጠንካራ ህዝባዊ ትግል ከተፈቱት አንዱ የሆነው ዳንኤል ዮሃንስ ደብረ ታቦር ላይ መታሰሩ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የህወሓት የበላይነት በነገሰበት መከላከያ ውስጥ በኮማንዶነት ተመርቆ ያገለገለው፣ በመጨረሻም የለየለት ዘረኛ አካሄድን ባለመቀበሉ ከስራው የተባረረው ዳንኤል ዮሃንስ “አማራዊ ብሎም ሀገራዊ ለውጥ ያስፈልጋል፤ ሴረኛ እና ዘረኛ የጭቆና አገዛዝ በቃን” በማለት ከእነ ጌታቸው አዱኛ፣ ምስጋና ደምሴ፣ አሸናፊ ሞገስ፣ ሙሉቀን ባዘዘው፣ ኢ/ር ጌትነት፣ ታዴ ብርሃኑ እና ከእነ መሳፍንት ጋር በመሆን ባደረገው የትግል እንቅስቃሴ የተነሳ ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ 2 ዓመት ከ6 ወራት በአማራ ክልል እና በፌደራል እስር ቤቶች በግፍ ተሰቃይቷል። ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተመርቆ ለሀገሬ አገለግላለሁ በሚል በመከላከያ ሰራዊት ተሰልፎ በኮማንዶነት በመሰልጠን ለተወሰኑ ዓመታት ያገለገለው ዳንኤል ዮሃንስ የህወሓት መራሹ ዘረኛ አካሄድን ባለመቀበሉ ከስራው እንዲባረር መደረጉ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። በመቀጠልም የሂሳብ ምሩቅ በመሆኑ በደቡብ ጎንደር ዞን በሙጃ ወረዳ በመምህርነት ሲያገለግል ቆይቷል። የህወሓት አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ዘርፈ ብዙ ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ ሲመጣ የተመለከተው ዳንኤል ወደ ኤርትራ አቅንቶ ስርዓቱን ለመታገል በመወሰን ከእነ ጌታቸው አዱኛ፣ ምስጋና ደምሴ፣ አሸናፊ ሞገስ፣ ሙሉቀን ባዘዘው፣ ኢ/ር ጌትነት፣ ታዴ ብርሃኑ እና ከእነ መሳፍንት ጋር በመሆን ሁመራን አልፎ ኤርትራ ምድር ሊገባ ሲል ክብሮም በተባለ በሕወሓት ደህንነት ተይዞ ብዙ ግፍ ተፈጽሞበታል። ክብሮም በሚባለው የህወሓት ደህንነት ትዕዛዝ ሁመራ ላይ እጅ እና እግራቸው ታስሮ ውጭ ላይ ለ5 ቀናት በዝናብ፣ በብርድ እና በጸሀይ እያስመቱ በድብደባ ካሰቃዩ በኋላ ወደ ጎንደር የደህንነት ቢሮ በመላክ ለ3 ቀናት በጨለማ ቤት አቆይተው በ4ተኛው ቀን በሌሊት በመጫን ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ በመውሰድ ለ6 ወራት ያህል በምርመራ አቆይተዋቸዋል፤ የሀሰት ክስ መስርተውም ወደ ቂሊንጦ በመውሰድ ግፍ ሰርተውባቸዋል። ይሁን እንጅ ህዝባዊ ትግሉ እያዬለ መምጣቱን በግልጽ የተመለከተው ብዙ ሽህዎችን ማሰር እንደ ማፈኛ እና ዝም ማሰኛ፣ የስልጣን እድሜ መቀጠያ አድርጎ የቆጠረው የህወሓት ኢህአዴግ አገዛዝ ከ2 ዓመት ከ6 ወር በኋላ በ2010 ዓ/ም ከአባሪዎቹ ጋር የፈታው መሆኑ ይታወቃል። በደብረ ታቦር ከተማ የ04 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ዳንኤል ዮሃንስ ከእስር ከተፈታ ማግስት ጀምሮ ለአማራ ህዝብ ይጠቅማል ባለው አደረጃጀት ተሰልፎ አገልግሏል። ከእነዚህም መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች እና በወቅቱም የጠቅላላ ጉባኤ አባል በመሆን ሰርቷል። በመቀጠልም የአማራ ህዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚፈጸምበትን ወረራ ለመቀልበስ የፋኖነት ትግል የግዴታ አስፈላጊ ነው በማለት ከህልውና ትግሉ ጋር በተታያዘ ከእነ ፋኖ ደረጀ በላይ ጋር አብሮ በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፎ የታገለ ጀግና ነው ሲሉ ጓደኞቹ መስክረዋል። በዚህም በጋሸና ፣በጉና፣ በዳህና እና በዳውንት ግንባር አሸባሪውን ትሕነግ ፊት ለፊት የተዋጋ ስለመሆኑ የትግል አጋሮቹ ይናገራሉ። ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት የሆነው ዳንኤል አሁን ላይም በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የ2ኛ ዲግሪውን እየተማረ እንደነበርም ታውቋል። ይሁን እንጅ ምንጮች እንደሚሉት ዳንኤል ዮሃንስ አሁንም “ብልጽግ ነኝ፤ ታድሻለሁ” በሚለው አገዛዝም መሸለም ሲገባው ከመሳደድ እና ከመታሰር አልዳነም። ጥቅምት 24/2015 ንጋት ላይ በደብረታቦር ከተማ 04 ቀበሌ ከመኖሪያ ቤቱ እያለ ግልጽ ባልተደረገ ምክንያት በከተማው ፖሊሶች እና አድማ በታኞች ታስሯል። በደብረ ታቦር ከተማ በመጀመሪያ ወደ 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱትና አንድ ሰዓት ካቆዩት በኋላ ወደ አድማ ብተና ካምፕ ወስደውታል ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply