የህወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም…

የህወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ረፋድ እንደተናገሩት የጁንታው ትሕነግ አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል። የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚያገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል በአካል በመቅረብ ማሳወቅ አልያም በመከላከያ ሠራዊት የስልክ ቁጥር በ011 1 248573 መጠቆም እንደሚቻልም ተገልጿል። የከሃዲው ትሕነግ አመራሮች ተመተዋል፣ተይዘዋል፣ከሀገር ወጥተዋል፣ በተጨማሪም በምሽግ ውስጥ ናቸው በሚል ብዙ መረጃዎች ቢወጡም መንግስት አጣርቶ መረጃዎችን ለህዝብ ከማሳወቅ መቆጠቡ በራሱ እያነጋገረ ይገኛል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply