የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ጥቃት አሳፋሪና ሀገርን የመካድ ተግባር ነው ተባለ፡፡        አሻራ ሚዲያ    ህዳር፡- 4/03/2013 ባህር…

የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ጥቃት አሳፋሪና ሀገርን የመካድ ተግባር ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡- 4/03/2013 ባህር…

የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ጥቃት አሳፋሪና ሀገርን የመካድ ተግባር ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡- 4/03/2013 ባህር ዳር የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን የተንኮል ሴራውን በማስፋት ለሃገሪቱ ደጀን በሆነው የሃገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት ኢትዮጵያዊ ከሆነ ወገን የማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን በሀዋሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ተናግረዋል ። “ከኢትዮጵያ ባለፈ ለውጪ ሠላም በማስከበር ኩራትና መከታ የሆነው የሃገር መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ለህዝቡ እያከናወነ ያለው የልማት ተሳትፎ ሊያሸልመውና ሊያስወድሰው እንጂ ጥቃት ሊፈጸምበት አይገባም ነበር ብለዋል። “ለሃያ አመት የትግራይን ህዝብ ደህንነት ሲጠብቅ የኖረ መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የሀገር ክህደት ነው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡ “ለትግራይ ህዝብ በችግር ጊዜ የደረሰ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት የፈጸመው የጥቂት ሆድ አደር ቡድኖች ስብስብ የትግራይን ህዝብ አይወክልም” ብለዋል። በመጨረሻም በሐዋሳ የሚኖር የትግራይ ተወላጅ የወንጀለኞች መደበቂያ ሊሆን እንደማይችል መልክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply