የህወኃት ዋና ዋና ሀላፊዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋገጡ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ17፣ 2013ዓ.ም ባህርዳር) ጀኔራሉ ለኢሳት በስልክ እንደገለፁት ብዙዎቹ የህወኃት ከፍ…

የህወኃት ዋና ዋና ሀላፊዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋገጡ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ17፣ 2013ዓ.ም ባህርዳር) ጀኔራሉ ለኢሳት በስልክ እንደገለፁት ብዙዎቹ የህወኃት ከፍ…

የህወኃት ዋና ዋና ሀላፊዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋገጡ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ17፣ 2013ዓ.ም ባህርዳር) ጀኔራሉ ለኢሳት በስልክ እንደገለፁት ብዙዎቹ የህወኃት ከፍተኛ አመራሮች ተደምስሰዋል፡፡ ነገር ግን ማን እና እንዴት የሚለውን በቅርብ እናሳውቃለን ያሉ ሲሆን፣በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ አንዳንዶች ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ህዳር 27 ቀን 2013 ዓም በተምቤን አካባቢ እንደተያዙ እየተናገሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጌታቸው ረዳ በቲዊተር ገፃቸው ከሰሞኑ አልሞትኩም፣አለሁ ብለው ፅፈዋል፡፡ ነገር ግን ቲውተሩ በትክክል የእሳቸው ስለመሆኑ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡… የአሻራ ምንጮች እንደነገሩን ግን የህወኃት አመራሮች ቢደመሰሱም፣ ሽምቅ ውጊያው ሊቀጥል እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ በሌላ በኩል በሱዳን የሚገኙ ተፈናቃይ የትግራይ ተወላጆች የህወኃት አመራሮች ወደ ስልጣናቸው ካልተመለሱ እኛም ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ብለዋል፡፡ ነገር ግን ወደ ሱዳን የሸሹ አካላት ብዙዎች የማይካድራን ጭፍጨፋ የመሩ እንዳሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡ በማይካድራ ከአንድ ሺ አንድ መቶ በላይ ሰዎች በግፍ መጨፍጨፋቸውን የኢሰመጉ መግለጫ ያሳያል፡፡ አንዳንድ በሱዳን የሚገኙ ተፈናቃዮች ከሱዳን ሀይል አብረው የኢትዮጵያን አርሶአደሮች እየወጉ መሆኑም እየተነገረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከኮንሶ ህዝብ ሞት እና መፈናቀል ጀርባ ኦነግ እንዳለበት ማረጋገጡን የኮንሶ የሀገር ሽማግሌዎችን ጠቅሶ ኢሳት ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply