የህወኃት ዘራፊ ቡድን ሀገር ለማተራመስ ሲዘጋጅባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በሁመራ ግንባር ተያዙ

የህወኃት ዘራፊ ቡድን ሀገር ለማተራመስ ሲዘጋጅባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በሁመራ ግንባር ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የተባበረ ክንድ የጦር ሜዳ መነጽርን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መያዛቸውን የ23ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ኮሉኔል አየለ ቢክቱ ቱፋ ገለጹ፡፡
 
ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች መካከል የጦር ሜዳ መነጽርን ጨምሮ ሞርታር 82 ብዛት ሁለት፣ ሞርተር 60 ብዛት ሰባት፣ ስናይፐር አንድ፣ ኤም 14 ጠበንጃ ብዛት 10፤ ተተካይ መትረየስ ሰባት፣ ተተካይ ክላሽ ስምንት ይገኙበታል፡፡
 
እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት የእጅ ቦንብ 102፣ ክላሽ 94፣ የክላሽ መጋዘን 202፣ ኤስኬስ 41፣ የመትረየስ ሰንሰለት30፣ የስናይፐር ጥይት 5ሺህ፣ የክላሽ ጥይት 8 ሺህ፣ ላውንቸር 3፣ የላውንቸር ጥይት (ቅንቡላ) 38 ፣ የመትረየስ ጥይት 4ሺህ 500፣ ከመካከለኛ እስከ ረዥም ርቀት የራዲዮ መገናኛ 26፣ የሞርተር ጥይት 108፣ የተለያዩ አልባሳት እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ጨምሮ መያዛቸውን ነው የተናገሩት፡፡
 
 
አሸባሪው የህውሃት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጉዳት ካደረሰ በኋላ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥፋት ለማድርስ የተዘጋጀ መሳሪያ መሆኑን የ23ኛ ክፍለጦር ሁለተኛ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አየለ ገልጸዋል፡፡
 
ምክትል አዛዡ ከመከለካያ ሰራዊት በተጨማሪ የአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ ላደረገው ተጋድሎ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

The post የህወኃት ዘራፊ ቡድን ሀገር ለማተራመስ ሲዘጋጅባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በሁመራ ግንባር ተያዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply