
#የህዝበ ሙስሊሙን ቤት የረበሸ መንግስት ወደኛ ቤትም ገብቶ ፍላጎቱን አሳክቷል!ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደትንሳኤ አባተ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የሃይማኖት ተቋማት እንደ ሌላው ዓለም በነፃ ካልተንቀሳቀሱ የከሰሩ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ እየሆኑ ይሄዳሉ። ህዝበ ሙስሊሙን ድምፅ አልባ ሲያደርጉ ተቀዳሚ ሙፍቲህን ብልፅግና በኢብራሂም ቱፋ ሲተካ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አልነቃም ነበር። ይህው በመቶ ሺህ የሚቃረብ ሙስሊም ሀገርህ አይደለም ተብሎ ከወለጋ ተፈናቅሎ ሀገር አልባ ሁኖ የሰቆቃ ህይዎት እያሳለፈ ነው ያለው። ኢብራሂም ቱፋ የተፈለገው ለዚህ ነበር። በለገጣፎ ብቻ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አስራ ሶስት መስጊዶች ተቃጥለዋል። ማንም ምንም አላለም። የሙስሊም ምሁራንና ኡስታዞች ነን እያሉ የሚጨፍሩ ሰዎች የት እንደገቡ አይታዎቅም። በህዝብ ላይ የሚሰራው ድብብቆሽ ለጊዜ ሊያስክድ ይችላል። በፈጣሪ ዘንድ ግን ፍትህ ይዘገያል እንጅ ሁሉም ይጠየቃል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስም የዘንድሮው የርክበ ካህናት ስብሰባ በብልፅግና ታጅቦ በሸኔ የበላይነት ተጠናቋል። ህዝብ ክርስቲያኑ ካህናቱ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤትና ማህበረ ቅዱሳን ይመለከተኛል የሚል ሁሉ አንድ ሁኖ አንድ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ኮሚቴ አዋቅሮ ቤተ ክርስቲያንን ሀገርን የሚታደግ አንድ ጠንካራ ኮሚቴ አዋቅሮ ካልሄደ ነገ ከነገ ወዲያ አመት ባልሞላ ጊዜ ቤተ እምነቶችን የምናጣበት ጊዜ እሩቅ አደለም። ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ወደ አንድ መጥተን ጥንት አባቶቻችን አብረው ለሀገር ዋጋ እንደ ከፈሉ ሁሉ ያ ዘመን ዛሬ ነው። አንድ ከሆን ሃይማኖታችንንም ሀገራችንንም ከጨካኞች እጅ ማዳን እንችላለን። ዝም ካልን ግን የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አናመልጥም። ኢትዮጵያ እና ህዝቦቷን እግዚአብሔር ይባርክ። ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post