የህዝበ-ውሳኔው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል—ምርጫ ቦርድ!በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ሕዝበ-ውሳኔውንም በተሳካ መልኩ ለማከና…

የህዝበ-ውሳኔው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል—ምርጫ ቦርድ!

በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

ሕዝበ-ውሳኔውንም በተሳካ መልኩ ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ÷በደቡብ ክልል ሥር የሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ-ውሳኔ ስኬታማ ክንውን በቦርዱ በኩል በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በምርጫ ሂደት የሚያጋጥሙ ጉድለቶች የሚሻሻሉበት እና አፋጣኝ እርማት የሚወሰድበት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱንም ጨምረው ገልጸዋል።

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር የሚገኙና ህዝበ-ውሳኔ የሚካሄድባቸው ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) ናቸው፡፡

የሕዝበ- ውሳኔው የድምፅ አሰጣጥ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply