የህዝበ-ውሳኔው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል—ምርጫ ቦርድ!

በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

ሕዝበ-ውሳኔውንም በተሳካ መልኩ ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ÷በደቡብ ክልል ሥር የሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ-ውሳኔ ስኬታማ ክንውን በቦርዱ በኩል በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በምርጫ ሂደት የሚያጋጥሙ ጉድለቶች የሚሻሻሉበት እና አፋጣኝ እርማት የሚወሰድበት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱንም ጨምረው ገልጸዋል።

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር የሚገኙና ህዝበ-ውሳኔ የሚካሄድባቸው ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) ናቸው፡፡

የሕዝበ- ውሳኔው የድምፅ አሰጣጥ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply