«የህዝብና ቤት ቆጠራ መርሃ-ግብር በ2014 ዓም ይካሄዳል» ሲል የማዕከላዊ ስታትስቲክ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አ…

«የህዝብና ቤት ቆጠራ መርሃ-ግብር በ2014 ዓም ይካሄዳል» ሲል የማዕከላዊ ስታትስቲክ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አ…

«የህዝብና ቤት ቆጠራ መርሃ-ግብር በ2014 ዓም ይካሄዳል» ሲል የማዕከላዊ ስታትስቲክ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለሦስት ጊዜያት የተራዘመው የኢትዮጵያ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። የኤጀንሲው ዋና ሃላፊ አቶ ቢራቱ ይገዙ የቆጠራው መርሃ ግብር በ2014 ዓም በሚመሰረተው አዲስ መንግሥት ተፈጻሚ እንደሚሆን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የህዝብ ቆጠራው በያዝነው 2013 ዓም በግንቦት መጨረሻ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ አስቀድሞ ቢደረግ ይመረጥ እንደነበር ሃላፊው ገልፀዋል። ሆኖም የቤት ለቤት ቆጠራው ባይከናወንም የህዝብ ቆጠራ ትንቢያን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ችግሮች ማቃለል ይቻላል ብለዋል። DW እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply