You are currently viewing የህዝብ ብሶትን ይበልጥ ማቀጣጠል እና የመዉደቂያ ጊዜን ማፋጠን ===== ሸንቁጥ አየለ ==== ብዙዎች ለህዝባችን ድምጽ ስለሆኑ ብቻ ታፍነዋል።አባይ ዘዉዱ አንድ ሆኖ ብዙ  የሆነ ጋዜጠኛ የህ…

የህዝብ ብሶትን ይበልጥ ማቀጣጠል እና የመዉደቂያ ጊዜን ማፋጠን ===== ሸንቁጥ አየለ ==== ብዙዎች ለህዝባችን ድምጽ ስለሆኑ ብቻ ታፍነዋል።አባይ ዘዉዱ አንድ ሆኖ ብዙ የሆነ ጋዜጠኛ የህ…

የህዝብ ብሶትን ይበልጥ ማቀጣጠል እና የመዉደቂያ ጊዜን ማፋጠን ===== ሸንቁጥ አየለ ==== ብዙዎች ለህዝባችን ድምጽ ስለሆኑ ብቻ ታፍነዋል።አባይ ዘዉዱ አንድ ሆኖ ብዙ የሆነ ጋዜጠኛ የህዝባችን እዉነተኛ ድምጽ ነዉ።… ከእዉነት ዉጭ አንዳች ሃሰት ዘግቦ አያዉቅም። ክርስቲያን ታደለ እዉነተኛ ሰላማዊ ታጋይ ነዉ።ለህዝቡ ድምጽ ከመሆን ዉጭ የሰራዉ በደል የለም። ሁለቱን ለምሳሌ አነሳሁ እንጂ የህዝብ ልጅ ጀግኖቻችን እጅግ ብዙ ናቸዉ። አረመኔዉ የአቢይ አህመድ ኦነግ/ኦህዴድ የህዝብ ልጆችን ማጎሪያ ቤት ቢከታቸዉም ህዝብ ፋኖን አምጦ ወልዷል። እንደ አባይ ዘዉዱ አይነት ንጹሃን ሰላማዊ ጋዜጠኞችን እንዲሁም በሰላማዊ ትግል መስክ የተሰማሩ ብዙ ጀግኖችን በማፈን የሚቀዬር የህዝብ ትግል ፈጽሞ አይኖርም። አረመኔዎች የሚሻላችሁ የህዝብ ድምጽ የሆኑ ንጹሃን ጋዜጠኞችን መፍታት፡ እንዲሁም እዉነተኛ የሰበአዊ መብት ታጋዮችን እና ንጹሃን ሰላማዊ ታጋዮችን መልቀቅ ነዉ።ከዚህ ዉጭ የህዝብ ብሶትን ይበልጥ ማቀጣጠል እና የመዉደቂያ ግዜአችሁን ማፋጠን ነዉ። ንጹሃን ጋዜጠኞች፡ እዉነተኛ የህዝብ ልጆች ፡ ቆራጥ የሰላማዊ ትግል አራማጆች እና የሰበአዊ መብት ተሟጋቾች ምንም እንኳን ያለ ወንጀላችሁ ታፍናችሁ እስር ቤት ብትሆኑም ድሉ የህዝባችሁ ነዉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply