የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡ (አሻራ ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም)  ባለፈው ሳምንት  የመተከል ጅምላ ጭፍጨፋ  በፀጥታ ያለፈው የምክርቤት ጉባዔ በነገ ሀሙሱ ገ…

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡ (አሻራ ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም) ባለፈው ሳምንት የመተከል ጅምላ ጭፍጨፋ በፀጥታ ያለፈው የምክርቤት ጉባዔ በነገ ሀሙሱ ገ…

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡ (አሻራ ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም) ባለፈው ሳምንት የመተከል ጅምላ ጭፍጨፋ በፀጥታ ያለፈው የምክርቤት ጉባዔ በነገ ሀሙሱ ገዳዮን ይመለከተዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ አሃዱ ራዲዮ እና ቴሌቬዥን እንደዘገበው በነገው የምክርቤቱ ስብሰባ ኦነግ ሸኔ እና መሰረቱን ከሱዳን ብሉናይል ግዛት ያደረገው የቢሻንጉል ጉምዝ ነፃነት ግንባርን በሽብርተኝነት እንደሚፈርጅ ይጠበቃል፡፡ ምክርቤቱ በመተከሉ የግፍ ጭፍጨፋ ዙሪያ መረጃ ያጠናከረ ሲሆን አዳዲስ ውሳኔዎችን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአንድ ቀን 300 ንፁሃን፣ በወር ውስጥ ብቻ ከ600 በላይ ንፁሃን በግፍ ሲጨፈጨፉ ምክርቤቱ የሀዘን ቀን እንኳ አለማወጁ አስተዛዛቢ ሆኖ አልፏል፡፡ በጫካ ተደራርበው እንደ እንስሳ የተቀበሩ ንፁሃንን አስከሬናቸው እንኳን ክብር አላገኘም፡፡ የመተከል ተፈናቃዮች ቁጥር ከሁለት መቶ ሺ የዘለለ ሲሆን በርሃብ እና በሀዘን ውስጥ ሆነው በሜዳ ወድቀው ዛሬም ይገኛሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply