የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ስብሰባውካሄደ ያለው።
በመጀመሪያ አጀንዳው የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን÷ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

በምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር  ሲሆን ÷ በስብሰባው ላይ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽንን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በፕሬዚዳንቷ ንግግር ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመንግስታቸውን አቋም በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

The post የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply