የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በንፁሃን ዜጐች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በንፁሃን ዜጐች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዋጋ ቃንቃ ቀበሌ በንፁሃን ዜጐች ላይ በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጻል፡፡

ምክር ቤቱ በፌስ ቡክ ገጹ ይህን መሰል ወንጀል በተደጋጋሚ እየተፈፀመ የዜጐች ህይወት እየተቀጠፈ ይገኛል ብሏል፡፡

በመሆኑም በእነዚህ ስለሀገርና ስለሰው ልጆች ክብርና ስብዕና በሌላቸው ወንጀለኞች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለንም ነው ያለው ምክር ቤቱ፡፡

ምክር ቤቱ በእነዚህ የጥፋት ኃይሎችና አሸባሪዎች ላይ ለሚወስደው እርምጃ ሕዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የህዝቡን ደህነነትና ሰላም እንዲጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መግለጹን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

The post የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በንፁሃን ዜጐች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply