የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
 
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራ ልዑክ በአፋር ክልል በጎርፍ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እየጎበኙ ይገኛል።
 
በጉብኝቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3 ሚሊየን ብር ደጋፍ ያደረገ ሲሆን ድጋፉን አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።
 
በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልል መንግስታት ፣ የፌዴራል መንግስት ተቋማት ፣ በጎ ፈቃደኞች እና የግል ተቋማት በአይነት እና በገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

The post የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply