የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሸዋ የሚገኙ የጤና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሸዋ የሚገኙ የጤና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በጋራ በመሆን በምስራቅ ሸዋ የሚገኙ የጤና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ዓለም ፀሀይ ጳውሎስ ጋር በመሆን የቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የአደአ እና የሎሜ ወረዳ ጤና ጣቢያዎችን እንዲሁም የጤና ኬላዎችን የስራ ዕንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
የምክር ቤቱ አባላትና ሚኒስትሮቹ የጤና ተቋማቱን ዕንቅስቃሴና የአገልግሎት መስጫ አሰራርና መሰረታዊ የጤና እንክብካቤ አሃድን ከተመለከቱ በኋላ በጠንካራ ስራዎቻቸውና ባሉባቸው ችግሮች ዙሪያ ከጤና ተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል።
ከዚያም ባለፈ በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው የጤና አገልግሎት ማሻሻያ ተግባራት ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሸዋ የሚገኙ የጤና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply