የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  አባላት የህወሃት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ  በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አ…

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የህወሃት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አ…

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የህወሃት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስት ተገዶ የገባበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በቆራጥነት በመምራት የወሰደውን እርምጃም እንዲሁ አስደናቂ ስለመሆኑ የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የህወሐት እኩይ ተግባር ለማክሸፍ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ለሰሩት ስራ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። የምክር ቤቱ አባላት በማይካድራ ላይ ዘርን መሰረት አድርጎ ዘግናኝ የንጹሃን ዜጎች ግድያ የፈፀመው ቡድኑን በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጠይቀዋል። የህወሃት የጥፋት ቡድን የትግራይ ህዝብ ውስጥ መሽጎ በመቅረት አሁንም ሌላ የጥፋት ስራዉን እንዳይቀጥል ለማድረግ መንግስት ምን አስቧል የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የህወሃት ቡድን ለፈጸማቸው እጅግ ዘግናኝ የዜጎች ጭፍጨፋዎች እና የሀገር ክህደት ተግባሮች ጉዳዩ በአለም አቀፍ ህግ ጭምር እንዲታይ የዲፕሎማሲ ስራ እየተሰራ ነው ወይ በሚልም ተጠይቋል። መንግስት እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች የተቀበሉት ቢሆንም አንዳንዶች ብዥታ እንዳላቸው ይገለጻል፤ በዚህ ላይ የማጥራት ስራውን ለመስራት ምን እንደታሰበ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮ መረጃ ኒውስ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply