የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የትህነግ ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ         አሻራ ሚዲያ      ህዳር 21/2013 ዓ. ም ባህር ዳ…

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የትህነግ ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ አሻራ ሚዲያ ህዳር 21/2013 ዓ. ም ባህር ዳ…

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የትህነግ ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ አሻራ ሚዲያ ህዳር 21/2013 ዓ. ም ባህር ዳር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትዛሬ ህዳር 21ቀን 2013 ዓ.ም 6ኛ (ስድሰተኛ )ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ (ሁለተኛ) ስብሰባውን ባከሄደበት ወቅት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ መንግስት ተገዶ የገባበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በቆራጥነት በመምራት የወሰደውን እርምጃም እንዲሁ አስደናቂ ስለመሆኑ የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የህወሐት እኩይ ተግባር ለማክሸፍ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ለሰሩት ስራ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። … የምክር ቤቱ አባላት በማይካድራ ላይ ዘርን መሰረት አድርጎ የተፈጸመው ዘግናኝ የንጹሃን ዜጎች ግድያ ቡድኑን በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጠይቀዋል። የህወሃት የጥፋት ቡድን የትግራይ ህዝብ ውስጥ መሽጎ በመቅረት አሁንም ሌላ የጥፋት ስራዉን እንዳይቀጥል ለማድረግ መንግስት ምን አስቧል? የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የህወሃት ቡድን ለፈጸማቸው እጅግ ዘግናኝ የዜጎች ጭፍጨፋዎች እና የሀገር ክህደት ተግባሮች ጉዳዩ በአለም አቀፍ ህግ ጭምር እንዲታይ የዲፕሎማሲ ስራ እየተሰራ ነው ወይ? በሚልም ጥያቄ ተነስቷል። መንግስት እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች የተቀበሉት ቢሆንም አንዳንዶች ብዥታ እንዳላቸው ይገለጻል፤ በዚህ ላይ የማጥራት ስራውን ለመስራት ምን ታስቧል? የሚል ጥያቄ ተነስቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በምክር ቤቱ አባለ፤ት የተነሱት ጥያቄዎች እና የጠቅላይ ሚኒስቴሩ መልስ ጠቅለል ብለው እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡- 1. ጽንፈኛው የህወኃት ቡድንና ኦነግ ሸኔን በአሸባሪነት ለምን አይፈረጁም? 2. ጁንታው የህወኃት ቡድን ሀገርን ለማፈራረስ ልዩ ሀይል ሲያሰለጥን እና ጸረ ሰላም ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መንግስት ከልክ ያለፈ ትዕግስት ለምን ማሳየት ፈለገ? 3. ጁንታው ህወኃት ቡድን ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አብሮ ወግቶናል እያሉ ፕሮፖጋንዳ መንዛት ጀምረዋል በዚህ ዙሪያ ያለው ትክክለኛ መረጃ ምንድን ነው ቢገልጹልን? 4. በተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችል ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና በመቋቋም በኩል መንግስት ያለው ዝግጁነት ምን ይመስላል? 5. አሁን እየተደረገ ያለው ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ቀደም ሲል በመንግስት በኩል እርምጃዎች ተወስደው ቢሆን ኖሮ አሁን የተፈጠሩትን አደጋዎች መቀነስ አይቻልም ነበር ወይ? 6. ከውጭ ወራሪ ሀይል ሊሰነዘርብን የሚችል ጥቃትን መመከት የሚችል ሀይል አለን ወይ? 7. የህግ ማስከበር እንቅስቃሴው በምስኪኒ የትግራይ ህዝብ ላይ አደጋ እንዳይደርስ እየተወሰደ ያለው ጥንቃቄ ምን ይመስላል? 8. እየተወሰደ ባለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ላይ በተፈጠረው ንቅናቄ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ምን እየተሰራ ነው? 9. ጁንታው የህወኃት በድን ሀገር ውስጥ አሉ ወይ ፤ካሉ ከተደበቁበት አውጥቶ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ ካለ? 10. አንድ ህገ ወጥ ቡድን ምን ምን መስፈርቶችን ሲያሟላ ነው በሽብርተኝነት የሚፈረጀው? 11. ጁንታው የህወኃት ቡድን ሀገር ለማፈራረስ ቅድመ ዝግጅት በሚያደርግበት ጊዜ መንግስት ለምን ቀድሞ መረጃውን ማግኘት አልቻለም፤መረጃው ከነበረውስ ለምን ቀድሞ ማክሸፍ አልተቻለውም? 12. ከጁንታው ህወኃት ቡድን ተንጠባጥበው የቀሩ አካላትን መንግስት ከስር መሰረቱ ለመንቀል ምን ስራ እየሰራ ነው? 13. ከሃዲው ቡድን በሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ አማካኝነት ለዘመናት ከቆየው ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለንን ወዳጅነት እክል እንዳይፈጥር ምን ስራ እየተሰራ ነው? የሚሉት ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ሁሉም ዕዞች አዛዦችና ምክትላቸው ሁሉም ከትግራይ ናቸው፤ 2. የኢትዮጵያ ሜካናይዝድ አዛዦች ሁሉም ከትግራይ ናቸው፤ 3. ከብርጌድ ጀምሮ እስከ መከላከያ ድረስ ሁሉም ከትግራይ ናቸው፤ 4. ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያን መገንባት ህግ መንግስቱ ያስገድደናል፤ 5. ወላይታና ሲዳማ እርስ በእርሱ አይገዳደለም ሰላም ፈላጊ ነው፤ይህን የሚያደርገው የጁንታው ታዛዥ ነው፤ 6. በሁሉም ክልሎች ግጭቶች ይፈጠራሉ በትግራይ ክልል ግን የለም፤ዋናው ተዋናዮቹ እነሱ ናቸውና፣ሰዎች ሞተዋል ግን አልተሳካላቸውም፣ሰዎች ተፈናቅለዋል ግን አልተሳካላቸውም፡፡ 7. ባለፉት 2 ዓማትት ተኩል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብቻ 37 ግጭቶች ነበሩ፤ይህ ሀይል እርስ በእርስ ጥርጣሬ እንዲፈጠርና ግጭት እንዲነሳ አድርጓል፤ግን ደግሞ ለኦሮሞ ህዝብ እቆረቆራለሁ ይላል፡፡ በአማራ ክልል 23 ግጭቶች ነበሩ አንዳንዱ በሀይማኖት ፤ 8. በአማራ ክልል ሰላም እንዳይኖር ቅማንትና አማራ እየተባለ ግጭቶች እንዲነሱ ስፖንሰር ተደርጓል፡፡ 9. በቤንሻንጉል ክልል 15 ግጭቶች እንዲነሱ ተደርጓል፤በአዲስ አበባ 14 ግጭቶች ተፈጥረዋል፡፡ 10. አርቲስት ሀጫሉን በመግደል ግጭቱን በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች መካከል ለማድረግ ብዙ ጥረት ተደርጓል፡፡ 11. በጋምቤላ የስደቶች መጠለያን ጨምሮ 7 ግጭቶች እንዲነሱ ሆኗል፤በደቡብም እንደዚሁ 12. የትግራይን ህዝብ አማራ ሊወጋህ ነው፤የፌደራል መንግስት ሊወጋህ ነው እንዲሁም ኤርትራ ልትወጋህ ነው እያሉ ጭንቀት ውስጥ እንዲገባ አደረጉት፤ 13. ከለውጡ በፊት በመከላከያ ሚኒስትር 80 በመቶ በሀላፊነት ደረጃ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ነበሩ፤ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply