የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ውይይት አደረጉ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሥራ እንቅስቃሴ እና የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያናን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው የተቋሙን አሰራር እና የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በወቅቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉትንግግር÷ የውጭ ጉዳይና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እና የተጠሪ ተቋማት ላይ በሚያደርገው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ሚኒስቴር የመስሪያ ቤታቸው የሰው ሃብትን በአግባቡ ስራ ላይ ለማዋል እና አሰራሮችን ለማሻሻል ግብኣት የሚሆኑ ሀሳብ የሚገኝበት መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታዋ አያይዘውም የውጭ ግንኙነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴና የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለመለየት ያስችላል ብለዋል።

ይህም ጠንካራውን ጎን ይበልጥ ለመገንባትና ደካማ ጎኖችን ለማስተካከል የሚያስችል ውይይት እንደሚሆን እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የኢንስቲትዩትን የስራ አፈጻጸም በኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አምባሳደር አረጋ ሃይሉ ሪፖርት ቀርቧል።

በሪፖርቱም ኢንስቲትዩቱን የተቋቋመበት ዋና ዓለማ፣ እስከአሁን ያከናወናቸው ሥራዎች፣ የሰጣቸው የስልጠና ዓይነቶች፣ አሁን ያለበት ደረጃ፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እና ለወደፊቱ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን በዝርዝር አቅርበዋል።

በመጨረሻ በቋሚ ኮሚቴው አባላት የቀረቡትን አስተያየትና ለተነሱ ጥያቄዎች አምባሳደር ብርቱካን እና የኢንቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር አምባሳደር አረጋ ኃይሉ መልስና ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ውይይት አደረጉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply