የህዩማን ራይትስ ዋችን ክሥ ኢትዮጵያ አስተባበለች

በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል እየታየ ላለው የሰብዓዊ ዕርዳታ መስተጓጎልም ሆነ ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ብቸኛ ተጠያቂው “አሸባሪው ቡድን ነው” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከስሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት ብቻ አሥር አምባሳደሮች ለሃገሪቱ ፕሬዚዳንት የሹመት ደብዳቤዎችን ማቅረባቸው ለተፈጠረው መረጋጋት እማኝ ነው ብለዋል የመሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ተወላጅ በሆኑ ከስደት ተመላሾች ላይ ግፍ ይፈፀማል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ ያሰፈረውን ክስ “ድርሰት ነው” ሲሉ ቃል አቀባዩ አስተባብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply