የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ከመንግስት ጎን በመሆን እንደሚሰሩ ፖለቲከኞች ተናገሩ

የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ከመንግስት ጎን በመሆን እንደሚሰሩ ፖለቲከኞች ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴ ግድቡን ለማጠናቀቅ ከምንግዜውም በላይ  ከመንግስት ጎን በመቆም  እንደሚሰሩ የተለያዩ ፖለቲከኞች ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ሌንጮ ለታ፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጣሂር መሃመድ እና የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ማሃበራት ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ÷ በቅርቡ በህወሓት ውስጥ ባለው ስግብግብ ጁንታ በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመውን ክህደት አውግዘዋል።

ፖለቲከኞቹ ከሃሳብ ጀምሮ ለህዳሴው ግድብ ከሚያደርጉት ድጋፍ ጎን ለጎን የሃገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እንደተዘጋጁም ገልጸዋል።

በዚህም የዚህን ሃገር አፍራሽ ሴራ ለማክሽፍም ሆነ ለመመከት ከመንግስት ጎን እንቆማለን ብለዋል።

የህዳሴ ግድብም ሆነ ሃገራዊ ጥቅምን በማስከበር ረገድ የተጀመሩ ስራዎች ላይ ክፍተት መፍጠር እንደማይገባም አስረድተዋል፡፡

እንደ ሃገርም ሁሉም አንድ ላይ ሊቆም የሚችለው አጀንዳና ከምንም በላይ የኢትዮጵያ ህልውና፤ አንድነትና ዘለቄታዊ ጥቅም ሲታሰብ የህዳሴ ግድብ በይደር የሚተው አይደለም  ብለዋል።

ስለሆነም በህዳሴው ግድብም ሆነ በሃገር ሰላም ማስጠበቅ ከገዢው ፓርቲ ጎን መቆም እንደሚያስፈልግ  ገልጸዋል።

አያይዘውም የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ እና ድጋፉም እስከመጨረሻው እንደሚቀጥልም ነው የተናገሩት።

በህዳሴ ግድብም ሆነ በሰላም ጉዳይ አንደራደርም የሚሉት ፖለቲከኞቹ ግድቡ እንዲጠናቀቅ የጀመሩትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ በመደገፍ ሃገር ለማፈረስ እና የህዝቦችን ሰላም ለማደፍረስ እያሴሩ የሚገኙ የህዋሓት ሴረኞች ተልዕኮን ለማክሸፍ  ዜጎች የየአካባቢያቸውን ሰላም አንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

The post የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ከመንግስት ጎን በመሆን እንደሚሰሩ ፖለቲከኞች ተናገሩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply