የህገ ወጡ ህውሓት ተላላኪ በሆነው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑ ተገለፀ

የህገ ወጡ ህውሓት ተላላኪ በሆነው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጂንታው ህውሓት ተላላኪ በሆነው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስመራ ኢጃራ ተናገሩ፡፡

የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስመራ ኢጃራ በኦሮሚያ ክልል በአራትም የወለጋ ዞኖች ህብረተሰቡን የሚዘርፈው እና የሚያሰቃየው የኦነግ ሸኔ ቡድን ሙሉ በሙሉ የሎጀስቲክስ ድጋፍ እና ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች የጂንታው ህወሓት ቡድን ነው ብለው፡፡

የጂንታው ቡድን ለ27 አመታት ሃገሪቱን ሲመሯት በራሳቸው ምህዋር ውስጥ በማሽከርከር ሲፈልገው በጎጥ ሲያሻው በቋንቋ በመከፋፈል ሃገራዊ አንድነት ሲያናጉ ቆይተዋል ብለዋል፡፡

የኦነግ ሸኔ ቡድን በጫካ በመሆን የአርሶ አደሩን ንብረት በመዝረፍ እንዲሁም ዘርን እና ቋንቋን መሠረት በማድረግ ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ ሠውን ይገድል ነበረ ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪ አያይዘውም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተጀመረውን ህግን የማስከበር ዘመቻ በተጀመረበት ጊዜ በኦሮሚያ በወለጋ በአራቱም ዞኖች የጂንታው ተላላኪ በመሆነው የኦነግ ሸኔ ቡድንን ለአንዴ ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት የክልሉ ልዩ ሃይል እና የሃገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላት በመቀናጀት አበረታች ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

የምስራቅ ወለጋ ዞን የፀጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ አባይ በበኩላቸው የጂንታው ህወሓት ቡድን እየተደመሰሰ ሲመጣ እና የሃገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላትና የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በወሰዱት እርምጃ በምስራቅ ወለጋ ዞን አስተማማኝ ሠላም ማስፈን ተችሏል ብለው፡፡

በዞኑ ውስጥ በተደረገ የሶስት ሳምንት ዘመቻ ብቻ በአና ጊዳ ወረዳ 4ክላሽ – 12 ሽጉጥ- 1ኤፍ ዋን ቦንብ – በዲጋ ወረዳ ደግሞ 1 ሺኅ 500 ሀሰተኛ የብር ኖታዎች፣ 132 የክላሽ ጥይቶች እና አንድ የጦር ሜዳ መነፅር መሳሪያዎች ከኦነግ ሸኔ ቡድን መማረክ መቻሉን ከምዕራብ ዕዝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የምዕራብ ዕዝ ህብረት ዘመቻ ሃላፊ ተወካይ ኮሎኔል ፋሲል ይግዛው በበኩላቸው የምዕራብ ዕዝ ማዘዣውን ነቀምቴ ካደረከበት ጊዜ ጀምሮ ከኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት ጋር በመቀናጀት የኦነግ ሸኔ ቡድንን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እየደመሰስን እንገኛለን ብለዋል፡፡

The post የህገ ወጡ ህውሓት ተላላኪ በሆነው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply