የህግ ማስከበር ዘመቻውን የተሳሳተ ትርጓሜ የመስጠት ዝንባሌ እንዳለ ተገለፀ

የህግ ማስከበር ዘመቻውን የተሳሳተ ትርጓሜ የመስጠት ዝንባሌ እንዳለ ተገለፀ

የአዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ የተሳሳተ ትርጓሜ የመስጠት ዝንባሌ እንዳለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ህግን የማስከበር ዘመቻን አስመልክቶ በሚተላለፉ የተሳሳቱ መልእክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ማብራሪያ ከሰጠባቸው ጉዳዮች ውስጥም “ኢትዮጵያ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እየገባች ነው” የሚለው አንዱ ነው።

የህግ ማስከበር ዘመቻው ግልፅ እና የተወሰነ ግብ ያለው ነው ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ፥ ዋናው አላማውም የፅንፈኛው ህወሓት አባላትን ለህግ ማቅረብ ነው፤  ዘመቻውም በቅርቡ ይጠናቀቃል ብሏል።

“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ከተሞችን እየደበደበ ነው እና ሰራዊቱ መቀሌን በአየር እየደበደበ ነው የሚለው ሌላኛው የተሳሳተ መሆኑን በመጥቀስ ማብራሪያ የሰጠበት ነው።

እንዲሁም “በመቀሌ ከተማ በሚካሄደው ዘመቻ ምህረት የለም” ተብሏል በሚል የሚሉ የተሳሳቱ ትርጓሜ የተሰጠባቸው መረጃዎች መሰራጨታቸውንም አስታውቋል።

The post የህግ ማስከበር ዘመቻውን የተሳሳተ ትርጓሜ የመስጠት ዝንባሌ እንዳለ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply