ማህበሩ ከተቋቋመበት 1987 አንስቶ ከ3 መቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች ነፃ የህግ አገልግሎት መስጠት መቻሉን የህግ ባለሞያ ሴቶች ማህበር ፕሮግራም ማናጀር ወ/ሮ ቤተልሄም ደጉ ተናግረዋል።
ማህበሩ ከዚህ በተጨማሪም በየመቱ 20 ሺህ ለሚሆኑ ሴቶቾ ተመሣሣይ የህግ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የፕሮግራም ማናጀሯ ገልፀዋል።
አሁንም በርካታ ተግባራትን እየከወነ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ማህበሩ ነፃ የህግ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ሴቶች በ”7711″ የስልክ መስመር መደወል ይችላሉ ብሏል።
የሚሰጠው ነፃ የህግ ማማከር አገልግሎት ሴቶች የተሻለ የህግ መረዳት ኖሯቸው እራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ የሚረዳ እንደሆነ ተገልጿል ።
በተጨማሪም የአቅም ግንባታ ስራዎች እና ሴቶች በፖለቲካዊ ተሳትፎ እራሳቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን እድል እንዲያገኙ ማህበሩ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 01 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post