የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ኤክስፖ ሊዘጋጅ ነው።በሀገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ከሆቴሎች ጋር የሚገናኙበት ኤክስፖ በኤሊያና ሆቴል አዘጋጅነት ሊካሄድ ነው ።አሁን በሀገ…

የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ኤክስፖ ሊዘጋጅ ነው።

በሀገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ከሆቴሎች ጋር የሚገናኙበት ኤክስፖ በኤሊያና ሆቴል አዘጋጅነት ሊካሄድ ነው ።

አሁን በሀገራችን ባለው የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ላይ ተደምሮ ትንንሽ ነገሮችን ሳይቀር ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገባበት በዚህ ሁኔታ ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች ጋር በጋራ የሚሰራበት ሂደት እንደሚፈጠር ተገልጿል ።
ኤክስፖው በተለይ አቅራቢዎችና ገዢዎች ፍላጎታቸውን ፣አገልግሎታቸውን በቀላሉ ለማሟላት ፣ ከሆቴል ኢንዱስትሪ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ምርታቸውን ለማስተዋወቅ እና የሆቴል ፍላጎትን እና አቅርቦትን በአንድ ቦታ እና እንደ ሀገርም የውጭ ምንዛሬ ችግርን ለመቅረፍ ያተኮረ ነው ተብሏል።

የሆቴል ማሰልጠኛ ተቋማት፣ባንኮች ፣ የኢንሹራንስ ፣ አየር መንገድ፣ ትራንስፖርት ፣ የምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ አቅራቢዎች የሚሳተፉበት ነው ተብሏል።
ከኮቪድ በኋላ የተዳከመውን የሆቴል ኢንዱስትሪ ለማነቃቃት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።

ሐምሌ 12 እና 13 በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች እና ከ10 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply