የለውጡ መንግስት ብሄረሰቦችን  ይሰለቅጥ ይሆን?! (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም)  ኢትዮጵያን እንደ ቅቤ እንጣት አለን በሚለው ጃልመሮ እና ፖለቲካ ቁማር ነው  እያጭበረበርን ኢትዮጵያን…

የለውጡ መንግስት ብሄረሰቦችን ይሰለቅጥ ይሆን?! (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም) ኢትዮጵያን እንደ ቅቤ እንጣት አለን በሚለው ጃልመሮ እና ፖለቲካ ቁማር ነው እያጭበረበርን ኢትዮጵያን…

የለውጡ መንግስት ብሄረሰቦችን ይሰለቅጥ ይሆን?! (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም) ኢትዮጵያን እንደ ቅቤ እንጣት አለን በሚለው ጃልመሮ እና ፖለቲካ ቁማር ነው እያጭበረበርን ኢትዮጵያን የኛ ብቻ እናደርጋለን ለሚለው ሽመልስ አብዲሳ መንፈስ ተሸካሚ የሆነው ብልፅግና ለአናሳ ብሄረሰቦች ስጋት ሆኗል፡፡… ባህልን በማጥፋት መሰረቱን ያደረገው የኦነግ ፖለቲካ በተለይ ለሀደሬ፣ ለሽናሻ፣ለጌዲዮ፣ለአኝዋክ ወዘተ የስጋት ምንጭ ሆኗል፡፡ የሀደሬዎች ሀረር በኦሮሚያ ብልፅግና ሙሉ በሙሉ የገባች ሲሆን፣ ጋምቤላም ወደ ደቡብ ሱዳን ለመገናኘት በሚል ወረራ ተፈፅሞበታል፡፡ የኦነግ ትጥቅ በብልፅግና አማካኝነት በሞያሌ እና በጋምቤላ እንደሚገባም ብዙዎች ይጠረጥራሉ፡፡ ከቢሻንጉል በሁለት ዓመት ውስጥ ያሶ ወረዳን ኦነግ የተቆጣጠረ ሲሆን እስከ ድባጤ ድረስ ለመቆጣጠር የኦነግ እና የኦሮሞ ብልፅግና ሀይል ድብብቆሽ እየተጫዎቱ ነው፡፡ የሀገር መሪ ሆኖ ተሰይሞ እንደ ተቃዋሚ የራሱን መንግስት የሚቃወመው የኦነግ ቡድን መሰረቱን አዲስ አበባ ላይ አድርጎ ሀገር እንዳትረጋጋ፣መለስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄረሰቦችን ደግሞ ለመዋጥ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ የአሻራ ምንጮች እንደሚያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩም በቀጥታ የዚህ ፕሮጀክት ደጋፊ ሲሆኑ፣ ለዚህ አስፈፃሚዎችንም በቤተመንግስት በአማካሪነት ደርድረዋል፡፡ ከአማራ ሆን ተብሎ ምንም ሚና የሌለውን ዳንኤል ክብረትን በቤተመንግሥት እያሳዮ አማራ ተወክሏል የሚሉት የብልፅግና ሰዎች የእነ ዳኔኤል ስልጣን ግን መግለጫ በተረት ቀላቅሎ ከመፃፍ የዘለለ አይደለም ብሎናል ምንጫችን፡፡ ቤተመንግስቱ በሙሉ፣ሪፐፕሊካን ጋርዱ በጠቅላላ፣ደህንነቱ እና የወታደር ማዘዣዎች በአንድ አካባቢ የተያዙ ሲሆን እሾህ ተነቅሎ እሾህ የተተከለበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መጪው አስጊ እንደሆነ የፖለቲካ ግምገማዎች ያሳያሉ፡፡ የአማራ ብልፅግና አውርቶ አደሮች እና የአድርባዮች ማህበር መሆኑ የሀገሪቱ ፖለቲካ እንዲዛነፍ አድርጓል፡፡ የአማራ ብልፅግናዎች ሲሾሙም ሆነ ሲሻሩ እንኳ መረጃ እንደ ሌላቸው አሻራ አረጋግጧል፡፡ አንዳንድ የአማራ ብልፅግናዎች ከብልፅግና እንነጠል ቢሉም፣ሁሉም በአንድ ልብ ለመስማማት ግን ተቸግረዋል፡፡ የአማራ ብልፅግና በክልል እና በፌዴራል አመራሮች መካከል አለመናበብ የነበረ ሲሆን፣አሁን ላይ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply