የሉሳካ ከተማ ከንቲባ የከተማዋ ነዋሪዎችን በስታዲየም ባዘጋጆት የሰርግ ስነስርአታቸው ላይ እንዲታደሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዛምቢያ መዲና ሉሳካ ከንቲባ ሰርጋቸውን በከተማዋ ስታዲየም ውስጥ ለማካሄድ አቅደዋል፡፡ ይህ እቅዳቸው ግን ውዝግብ አስነስቷል፡፡ ሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወቅት እንዲተገበሩ ከደነገገቻቸው ህጎች መካከል ደግሞ ሰርጎች በ50 ሰዎች ብቻ መወሰን አለባቸው የሚል ነው፡፡

ከንቲባው ሚልስ ሳምፓ ይህንን ህግ ከምንም የቆጠሩት አይመስልም እንደ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ፡፡ በቢቢሲ ፎከስ በአፍሪቃ ሬዲዮ ላይ በነበራቸው ቆይታ “የሉሳካ ሰዎች በሠርጌ ላይ ለመሳተፍ እንደሚፈልጉ ነግረውኛል ይህንን ደግሞ ማክበር እፈልጋሁ” በማለት ተናግረዋል ፡፡

ከንቲባው እንደተናገሩት በቤታቸው በተደረገው የቅድመ ጋብቻ ዝግጅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታድመው ነበር ፡፡ የኮሮናቫይረስ ደህንነት እርምጃዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም አክለዋል ከንቲባው፡፡ ሰዎች ወደ ስታዲየሙ ሲገቡ እጃቸውን በአግባቡ ይታጠባሉ፤የአፍና የአፍንጫ ማስክም ያደርጋሉ ደግሞም ማህበራዊ ርቀታቸውንም ይጠብቃሉ ነው ያሉት፡፡

ሰርጎን ስለምን ማዘግየት አልቻለም ተብለው ለቀረበላቸው ትችት “ኮሮና ቫረስ እስኪያበቃ ድረስ አልጠብቅም – ሙሽራዬ ጥላኝ ልትሄድ ትችላለች!” ብለዋል ፡፡ ዛምቢያ እስካሁን 18 ሺህ 456 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ስታረጋግጥ 369 ዜጎቿ ደግሞ በሞት አታለች፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በአፍሪካ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ117 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 800 በላይም ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከ72 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪዎችም በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ሕይወታቸውን ማጣታቸው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8

ያይኔ አበባ ሻምበል
ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply