የሊቢያ ም/ቤት ኮሚቴ የዓርቡን ምርጫ ማካሄድ አይቻልም አለ

የሊቢያ የምክር ቤት ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ከነገ በስቲያ ዓርብ ሊደረግ የታቀደውና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ማካሄድ የማይቻል መሆኑን አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ ኮሚቴ ሊቀመንበር ለፓርላማው መሪ በላኩት ደብዳቤ የምርጫውን ጊዜ ከማስተላለፍ ውሳኔ የደረሱት ስለምርጫው ከደረሳቸው የቴክኒክ ፍትህና ደህንነት ሪፖርቶች በመነሳት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ይሁን እንጂ የደረሷቸው ሪፖርቶች ምን ምን እንደሆኑ አላብራሩም፡፡ 

የሊቢያ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን ምርጫው እኤአ ወደ ጥር 24 እንዲተላለፍ ሀሳብ ማቅረቡ ተገልጿል፡፡ 

ሊቢያ የቀድሞ መሪ መሀመድ ጋዳፊ ከተወገዱ ወዲህ ላለፉት 10 ዓመታት በጊዚያው መንግሥት ስር የምትተዳደር መሆኑን ተመልክቷል፡፡ 

በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ጥሪ መሰረት፣ በምስራቅና ምዕራብ ያሉ አማጽያን ኃይሎች፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተኩስ ማቆም ስምምነት ቢያደርጉም፣ ሰሞኑን በትሪፖሊ አካባቢ አንዳንድ አማጽያን የኃይል እንቅስቃሴዎችን በማድረጋቸው ውጥረት መፈጠሩ እየተገለጸ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply