የላሊበላ ከተማ በሰላም ማጣት  ምክንያት ከጎብኚዎች ያገኝ የነበረውን 78 ሚሊየን ብር አጥቻለሁ አለበሰሜን ወሎ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ ጥላሁን አባተ እንደተናገሩት  በ6 ወ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/JcFJmqzBFBxRXhEnrdUcCYCFjHZ2XszBvYv1L7KOrSoIwDHo94x4wJAQ6YN6W4IQexl7Kkvya88Fapg6kGsPZObamj_6neMpm5fkJVz6yaAJyzcY9m73jYo-XEPO7g4Qib4bRz2PbjLWpq_n8D9pggQ2_SDJfEcekHeOhoEdCEll8Yz7ObO7YSOlXSVOe5d_tZgQoC_ESprbilJAQOmvZRpID5jEdT2lDUcOs-0BaUNNivyc0IeOsAJ-kFNxJBjm_3jH5GF4_Aw5yIPFS3Qdx9Zh73fAg83aQNzvNO66HP_Me26_UFU6I9nTWIPouqONeWh6O1h8u64GFQgJYJmJXg.jpg

የላሊበላ ከተማ በሰላም ማጣት  ምክንያት ከጎብኚዎች ያገኝ የነበረውን 78 ሚሊየን ብር አጥቻለሁ አለ

በሰሜን ወሎ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ ጥላሁን አባተ እንደተናገሩት  በ6 ወሩ 3 ሺህ 834 የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ስፍራው ያቀናሉ ተብሎ ቢጠበቅም መምጣት የቻሉት ግን 1 ሺህ 486 ብቻ ናቸው ብለዋል።

በእቅዳችን መሰረት ወደ  60ሺ ጎብኚዎች ይመጣሉ ተብሎ ታቅዶ እንደነበር እና 90ሚሊየን ገቢ ለማስገባት ቢታቀድም በሰላም እጦት ማሳካት እንዳልቻለ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል 1 ሚሊየን የሚጠጉ የሃገር ውስጥ ጎብኚዎችን ለማስተናገድ ታቅዶ 512 ሺህ ጎብኚዎችን ማስተናገድ  ተችሏል ብለዋል።

በሰላም እጦቱ ምክንያት ቤተ-ክርስቲያን ሆቴሎች አስጎብኚዎች፣ ትራንስፖርት ሰጪዎች፣ በጎብኚዎች ቁጥር ማነስ የሚያገኙት ገቢ መቀነሱም ተጠቁሟል።

በዚህም የላሊበላ ከተማ በሰላም እጦት ምክንያት ከጎብኚዎች ያገኝ የነበረውን ገቢ በተጠቀሰው ልክ ማጣቱ ተሰምቷል።

ለአለም አሰፋ

ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply