የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያን ጥገና በተያዘለት እቅድ እንደማይከናወን ተገለፀ፡፡

የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ አለሙ ለአሐዱ እንደገለፁት በሚያዚያ ወር ሊጀመር የነበረው የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያን ጥገና በተያዘው እቅድ መሰረት አይካሄድም፡፡

በየካቲት ወር ላይ ቅርስ የሚጠግኑ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ በሚያዚያ ወር ውቅር አብያተ ክርስቲያኑ ጥገና ይደረግለታል የተባለ ቢሆንም በታቀደው ጊዜ አንደማይጀመር ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

አክለውም ቅርሱ ጥገና የሚደረግለት በፈረንሣይ መንግሥት አማካኝነት ሲሆን ፈረንሣይ በኮቪድ-19 ምክንያት የሀገሯን እንቅስቀሴ ዝግ አድርጋለች፡፡ይህን ተከትሎም ከፈረንሣይ ይመጣሉ ተብለው የነበሩ ባለሙያዎች ሊመጡ አልቻሉም ብለዋል፡፡

በተጨማሪ የካቲት ወር ላይ ለቅርስ ጥገና ባለሙያዎች ስልጠና ይሰጣል ተብሎ የነበረው  በዚህ ምክንያት መሰረዙን ተናግረዋል፡፡

ቀን 08/08/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያን ጥገና በተያዘለት እቅድ እንደማይከናወን ተገለፀ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply