የላሊበላ ገዳም ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የድጋፍ አሰባሳ…

የላሊበላ ገዳም ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ ዲያቆን አንተነህ እሸቱ እንደገለጹት የላሊበላ ገዳም ወደነበረበት ለመመለስ በዘላቂነት መፍትሔ የሚሆነው በተቻለ ፍጥነት የሀገርን ሰላም እና የቱሪዝም ፍሰቱን ወደነበረበት መመለስ ነው። ግሸን በዓመት እስከ አንድ ሚሊየን ዜጎች እንደሚጎበኙት የጠቆሙት አስተባባሪው በላሊበላም የሀገር ውስጥ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት እንዲሁም ደብሩ መሰል ችግር ሲገጥመው መቋቋም የሚችልበት ቋሚ የገቢ ምንጮችን በሂደት ለመመስረት መታሰቡን አመላክተዋል። አስራ አንድ አብያተ-ክርስቲያናትን አቅፎ የያዘው ላሊበላ በውስጡ ከአንድ ሺሕ በላይ አገልጋይ ካህናት፣ ከ100 በላይ የቅርስ ጠባቂዎች እንዲሁም በላሊበላ ከተማ ልመና እንዲቀር ለማድረግ ያደራጃቸውና ከደብሩ በቀጥታ የሚደጎሙ አረጋዊያን ተጧሪዎች፣ ሕጻናት ከነወላጆቻቸው በድምሩ ከ10 ሺሕ በላይ በቀጥታ በገዳሙ የሚደጎሙ ዜጎች መኖራቸውንም አንስተዋል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply