#የላንቃና #የከንፈር መሰንጠቅ ችግር?የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፊት የሚከሰት የጤና እክል ነው፡፡ የላይኛው ከንፈር ተሰንጥቆ ወደ አፍንጫ ድረስ ሊሰፋ የሚችል ሲሆ…

#የላንቃና #የከንፈር መሰንጠቅ ችግር?

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፊት የሚከሰት የጤና እክል ነው፡፡ የላይኛው ከንፈር ተሰንጥቆ ወደ አፍንጫ ድረስ ሊሰፋ የሚችል ሲሆን፤ ህጻናት አፋቸው ሲከፈት ላንቃቸው ተሰንጠቅ ይስተዋል፡፡

የላንቃ እና የከንፈር መሰንቅ በሀገራችን ብሎም በዓለማችን የሚከሰት የጤና እክል እንጂ በእርግማን እንደሚከሰት ማሰብ ፍጹም ስህተት እና ሊታረም የሚገባ አረዳድ መሆኑን የዘርፉ ባሞያዎች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

በዚህም ምክንያት ህጻናት ከሚደርስባቸው የጤና እክል በተጨማሪም ለስነ ልቦና ጉዳት እንደሚዳረጉም ተጠቁሟል፡፡

የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ መነሻ ምክንያቱን ይህ ነው ማለት ባይቻልም ፤ የዘረመል እክል ፣ በእርግዝና ወቅት አልኮል መጠጣት እና ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም በእርግዝና ወቅት የሚወሰዱ መድሃኒቶች ለህመሙ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ናቸው ሲሉ የቀዶ ጥገና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር አማኑኤል ጠብቀው ተናገረዋል።

#የህመሙ ምልክተቶች
#የከንፈር መሰንጠቅ
• የከንፈር መሰንጠቅ ምልክቶች በቀላሉ የሚስተዋሉ ናቸው፡፡
በህጻናት የላይኛው ከንፈር ላይ መሰንጠቅ ይስተዋላል፡፡

#የላንቃ መሰንጠቅ ሲሆን፤
• የህጻናት አፍ ሲከፈት ላንቃ ተሰንጠቆ መስተዋል
• ህጻናት ጡት በሚጠቡበት ወቅት መቸገር በዚህም ምክንያት የክብደት መቀነስ
• ህጻናት ካደጉ በኋላ የመናገር ችግር መኖር

#ተጓዳኝ ችግሮች
• የልብ ህመም
• የአከርካሪ አጥንት ችግር ሊከሰት ይችላል
• የጆሮ እክል ያስከትላል
• መስማት ለመቀነስ
• ንግግርን አለመቻል ያስከትላል ተብሏል፡፡

የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የጤና እክል መሆኑን የሚናገሩት ባለሞያው፤ ህመሙ በህክምና የሚድን ቢሆንም ስለ ህመሙ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን ተከትሎ ይህ የጤና እክል ያለባቸው ህጻናት ህክምና እያገኙ አለመሆኑን ተናረዋል፡፡

በህመሙ የሚሰቃዩ ህጻናት ቁጥር አነስተኛ አለመሆን የተነገረ ሲሆን፤ በተለይም በክፍለ ሃገር የሚገኙ ህጻናት ላይ ከህመሙ በተጨማሪም የሚደርስባቸው ስነ ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጫናዎች ከፍተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

• በራስ መተማመን መቀነስ
• ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ መቸገር
• በወላጆች ላይ ከማህበራዊ ህይወት መገለል

#ህክምናው
የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ በጊዜ ህክምና ካልተደረገ የተሰነጠቀው የሰውነት ክፍል እየሰፋ ስለሚሄድ ቀዶ ጥገናውን አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በህጻናቱ ላይ ሁለቱም፤ ማለትም የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ተከስቶ ከሆነ በቅድሚያ የከንፈር መሰንጠቁን እንደሚታከም ነግረውናል፡፡

ከህመሙ ጋር አብረው ለሚወለዱ ህጻናት ከ10 እስከ 12 ወራት ውስጥ ቀዶ ጥገናው የሚከናወን ሲሆን፤ ከቀዶ ጥገና በፊት ባሉት 6 ወራት ውስጥ የተሰነጠቀው ላንቃ ባለበት እንዲቆይ በሰው ሰራሽ ፕላስቲክ ህጻናቱ እንዲመገቡ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በህክምናው ይህ የጤና እክል ያለባቸው ህጻናት በቀዶ ጥገና አማካኝነት ማውራት፣ መመገብ እና መናገር እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን፤ በተጨማሪም መልክን የመመለስ ስራ እንደሚከናወንም ተነግሯል፡፡

#የመከላከያ መንገዶች

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህመምን ቀድሞ ለመከላከል፤ በቅድሚያ አጋላጭ ሁኔታዎችን መቀነስ እንደሚገባ የገለጹት ባለሞያው፤ እርግዝና ከተፈጠረ በኋላ የእርግዝና ክትትል ማድረግ እና ህጻናቱ ከተወለዱ በኋላ አፋቸውን ከፍቶ ላንቃን መመልከት በዚህም ቀደም ሲል የተገለጹ ምልክቶቹን በህጻናቱ ላይ የሚስተዋሉ ከሆነ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት ይገባል ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply