You are currently viewing የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ እያደረገ ላለው አበረታች አስተዋፅኦ ከጠገዴ አርማጭሆና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር የእውቅና ስጦታ ተበረከተለት። አማራ ሚዲ…

የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ እያደረገ ላለው አበረታች አስተዋፅኦ ከጠገዴ አርማጭሆና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር የእውቅና ስጦታ ተበረከተለት። አማራ ሚዲ…

የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ እያደረገ ላለው አበረታች አስተዋፅኦ ከጠገዴ አርማጭሆና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር የእውቅና ስጦታ ተበረከተለት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጠገዴ አርማጭሆ እና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር በአርማጭሆ እና አካባቢው የሚሰተዋለው እገታ ፣የተደራጀ ወንብድና ፣ ዘረፋ ፣ጥይት ተኩስ ፣ የእርስ በርስ ግጭት ከአካባቢው እንዲጠፋ ብሎም በአካባቢው ተግባቦት፣አብሮነት፣ ወንድማማችነት፣ ልማትና እድገት እንዲሰፍን አልሞ የሚንቀሳቀስ ሲቪክ ማህበር ነው። ምንም እንኳ ከተመሰረት አጭር ጊዜ ቢሆነውም በርካታ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ አደረጃጀቶችን በመፍጠር፣ ህዝባዊ ምክክር በማድረግ እና መልካም የሚባሉ ማህበራዊ ተግባራትን በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል። የጠገዴ አርማጭሆ እና አካባቢው በጎ አድራጎት ማህበር ከተነሳበት አላማ አኳያ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚሰተዋለውን እገታ ፣የተደራጀ ወንብድና ፣ ዘረፋ ፣ጥይት ተኩስ ፣ የእርስ በርስ ግጭት ከአካባቢው እንዲጠፋ በማድረግ ረገድ በቆራጥነት እየሰራነው፤ አበረታች ውጤትም እያስመዘገበ ነው በሚል ለላይ አርማጭሆ ወረዳ የእውቅና ሽልማት አበርክቶለታል። የላይ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋፅኦም የ5 ሰንጋ በሬ ስጦታወች እና ለአሀዱ የባህል ቡድን ከመተማ ወረዳ የ10,00 ብር የገንዘብ ስጦታ ተበርክቷል። በፕሮግራሙ የአማራ እና የቅማንትን ህዝብ የጋራ አንድነት የሚያንፀባርቁ ስነ-ፁሁፎች የቀረቡ ሲሆን ሁለቱ ህዝቦች የጋራ ታሪክ ያላቸው ላይፋቱ የተጋመዱ መሆናቸውን የማህበሩ ሊቀ-መንበር አቶ አሰማራው መኮንን ገልፀዋል። አቶ አሰማራው ሲቀጥሉ የግብፅ ተላላኪወች በመካከላችን ልዩነቶችን በመፍጠር ጎንደርን የግጭት ቀጠና በማድረግ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጲያዊነትን ከስሩ ለመናድ የተደረጉ ሙከራዎች በተባበረ ክንድ ስለመክሸፋቸው ተናግረዋል። በሳለፍነው ሳምንት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅን በማገት ገንዘብ የሚዘርፉና የሚቀሙ 3 ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት መግለፁ ተዘግቧል፡፡ በላይ አርማጭሆ ወረዳ ከርከር እንዲብና ፣ጭላደወል እና በታች አርማጭሆ ወረዳ አጎራባች የገንበራ ቀበሌ ሚሊሻና ታጣቂዎች መስከረም 4 ቀን 2014 ዓ/ም በጋራ በመቀናጀት በሰው ልጅ እገታ ገንዘብ በመንጠቅና በመዝረፍ የተሰማሩ 3 ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ከሌሎች ካመለጡ ግብረ አበሮች ጋር ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ይታወሳል። ይህንን የጀብድ ስራም በትክል ድንጋይ ከተማ ማህበረሰብና የፀጥታ አካላት በጎዳና ላይ ፀያፍ ስራውን በማውገዝ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ በብሄር ስም የሚነግዱና የሚቀሙ የሚዘርፉ ጁንታና ጁንታዊ አስተሳሰብ ያላቸውን አካላት ህብረተሰቡና የፀጥታ አካላት ከመንግስት ጎን በመሆን በጋራ ለህግ የበላይነት መረጋገጥና ለኢትዮጵያዊ አንድነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በብሄር ሽፋን የሚነግዱ የሚዘርፉ የሚያግቱ ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ተግዳሮት የሚሆኑን በጋራ እንመክት ሲል የላይ አርማጭሆ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን መልእክቱን አስተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply