የልደቱ አያሌው ክስ ይሻሻል መባል

በልደቱ አያሌው ጉዳይ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሻሽል በማዘዝ፤ ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እውነታ የዋስትና መብት ላይ ብይን አልሰጥም አለ።

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችሎት ኅዳር 11 ልደቱ 4 ጠበቆች ጋር የቀረቡ ሲሆን፤ የመሀል ዳኛው የፍርድ ቤት ብይን ጽሑፍን የአማርኛ ትርጉም በንባብ ስለማሰማታቸው ፓርቲያቸው ኢዴፓ አስታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አዳነ ታደሰ፤ ችሎቱ በዐቃቤ ሕግ የተጠቀሱት 2 አንቀፆች ግልፅነት የሚጎላቸው በመሆኑ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ውሳኔ ማሳለፉን ገልፀዋል።ይሻሻል የተባለው ክስ ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለማፍረስ በማሰብ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት›› በሚል የተመሰረተባቸው ነው።

የተከሳሹን የዋስትና ጥያቄ በተመለከተ ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እና ባልተሻሻለበት ሁኔታ ብይን መስጠት አንችልም በሚል ውድቅ መደረጉንም ነው ያከሉት።

ልደቱምከታሰርኩ አራት ወር ሆኖኛል፤ የእስከዛሬው የፍርድ ቤት ሂደት የሚያሳየው ዐቃቤ ሕግ ዋና ዓላማው እኔን በወንጀል ከሶ የማስቀጣት ሳይሆን በተራዘመ የፍርድ ሂደት እኔን ማሰቃየት ነውሲሉ ቅሬታቸውን ማሰማታቸውን ፓርቲያቸው በፌስ ቡክ ገፁ ጽፏል።

ችሎቱም የተሻሻለውን ክስ ለመስማት ለኅዳር 24 ከቀኑ 8 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተሰምቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply