የሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦ በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማ…

የሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)

-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

– በመንገዳችን ላይ፦በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግን ብዙም ትኩረት ከማንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንድ ለየት ያለ ሀሳብን ያነሳል።

– ለጤናችን፦ በአዲስ አበባ በሱስ ላይ ከሚሰሩ ማገገሚያ ማእከላት ወደ አንዱ አቅንተን ቅኝት አድርገን ልናካፍላቹ የወደድነውን አዘጋጅተናል።

– በፍተሻ ሰዓታችን፦ የኢታስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች /አሽከርካሪዎች / ላይ ተደጋጋሚ የግድያ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ነዉ።

የሟች ወገኖች ፍትህን ከመንግሥት እየጠበቅን ነዉ ይላሉ፤

የቴክኖሎጂው ባለቤቶችስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ ?

በፍተሻችን ተመልክተነዋል።

-በኢትዮ ገበያችን ፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን ቁጥር እያሳደገ ይገኛል፤ አማራ ክልል ደግሞ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት ያለባቸው አካባቢዎችን ለይቻለሁ ብሏል።

ክልሉ በጥናቱ ምን ምን ማዕድናትን አገኘ? ከኢትዮ ገቢያችን ትሰሙታላችሁ።

-በዓለም ጉዳይ፦ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሰን ሸይኽ ሙሐመድ ሰሞኑን በግብጽ ካይሮ ጉብኝት ላይ ናቸው።

ከግብፁ አቻቸው አልሲሲ ጋር የመከሩት ሃሰን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አስገዳጅ ስምምነት ይፈረም የሚል አቋም ይዘዋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነዉ።

ለመሆኑ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ከኢትዮጵያ አንጻር እንዴት ይታያል?

የእለቱ የዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረት አድርጎበታል።

– እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply