የሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦ በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማ…

የሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)

-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

– በመንገዳችን ላይ፦ በመዲናችን አዲስ አበባ በየአካባቢው ያሉ ቆሻሻን ሰብስቦ በማስወገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ እያሰሙ ነው፤ አነጋግረናቸዋል።

– ለጤናችን፦ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 325 ሚሊዮን ሰዎች ከጉበት በሽታ ጋር ይኖራሉ፡፡

በበሽታዉ ኢንፌክሽን ምክንያትም በዓመት ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን ያጣሉ፤ብዙዎች ዝምተኛዉ ገዳይ ሲሉ የሚጠሩት ይህ የጉበት በሽታ ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ ይውላል፤ በጤና መሰናዷችን እንመለከተዋለን።

– በፍተሻ ሰዓታችን፦ ሩሲያ የኢትዮጵያ ወሳኝ አጋር እንደምትሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ምዕራባውያን የፍትህ ተቆርቋሪ ሊሆኑ አይችሉም ሲሉም ተደምጠዋል፤ ለምን?

በፍተሻችን ተመልክተነዋል።

-በኢትዮ ገበያችን ፦ ከጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከ180 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፤

የሲሚንቶ ግብይትና ሥርጭት መመሪያን በማይተገብሩ አካላት ላይ ደግሞ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፤
ከኢትዮ ገቢያችን ትሰሙታላችሁ።

-በዓለም ጉዳይ፦ አንድ ጉምቱ ዲፕሎማቷን ወደ ታይዋን ልትልክ የነበረችው አሜሪካ የቻይና ቁጣን ተከትሎ በድጋሚ አስብበታለሁ ብላለች።

ሁለቱ ሀገራት ዳግም መወዛገብ ጀምረዋል።

የእለቱ የዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረት አድርጎበታል።

– እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

የእለቱን ኢትዮ ማለዳ የምታቀርብላችሁ ያይኔአበባ ሻምበል ናት።

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply