የሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦ በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማ…

የሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)

-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

-በመንገዳችን ላይ መሰናዷችን ፦ብልሽት ገጥሟቸዉ እንዲሰሩ የሚሰጡ የሞባይል ስልኮች ለጠብ መነሻ እየሆኑ ነዉ፡፡
ስልኮችን እንዲሰሩ የሚሰጡ የኤሌክትሮኒክስ ባለሙያዎች እምነት ማጉደል ለችግሩ በምክንያትነት ተነስቷል፤ትሰሙታላችሁ፡፡

-ለጤናችን፦ በዓለማችን የአእምሮ ህመም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡
በአሜሪካ በፈረንጆቹ 2020 በተደረገ ጥናት ከ 5 ሰዎች መካከል አንዱ የአእምሮ ህመም ተጠቂ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የጤና ጉዳያችን በዚሁ የአእምሮ ህመም ላይ አተኩሯል፡፡

-በፍተሻ ሰዓታችን፦ በአንዳንድ ግለሰቦች ላይ የሚፈፀመው ህገ ወጥ እስር እና አፈና እንደቀጠለ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍም የደረሱት ጥቆማዎች አመላክተዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ጣቢያችን የመጣ ቅሬታን ይዘን የፍትህ አካላትን ምላሽ አካተን ጉዳዩን ፈትሸናል፡፡

-በኢትዮ ገበያችን ፦ የአማራ ክልል ምክር ቤት ለ2015 በጀት ዓመት ከ95 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡

በፋይናንስ ስርአት ያልተካተቱ ዜጎችን እንደሚያገለግል ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ አ.ማ አስታዉቋል፡፡

በኢትዮ ገቢያችን ትሰሙታላችሁ።

-በዓለም ጉዳይ፦ የቀድሞው የሩስያ ፕሬዝደንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ የዩክሬን ቀጣይ ካርታ ሲሉ ምስል አጋርተዋል፡፡
ሜድቬዴቭ ይፋ ያደረጉት ካርታ ዩክሬን ወደብ አልባ ያደረገ ከመሆኑ በላይ በርካታ ግዛቶቿን አንድም በሩስያ ሌላም በፖላንድ ግዛቶች ውስጥ የሚጠቃለሉ መሆናቸውን ያሳያል፡፡
የእለቱ የዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረት አድርጎበታል።

-እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

የእለቱን ኢትዮ ማለዳ የሚያቀርብላችሁ መሳይ ገ/መድህን ነዉ፡፡
እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

Source: Link to the Post

Leave a Reply