
የሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር ለቢቢሲ እንደገለፁት ምርጫ ቦርድ “ሕጋዊ አግባብን አልተከተለም፤ የሕግ ጥሰት ፈፅሟል” በማለት መክሰሳቸውን አስታውቀዋል። ፓርቲው ምርጫ ቦርድን የከሰሰው ከሐረሪ ክልል ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ አባላት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አባላት ምርጫ ላይ መሳተፍ አይችሉም የሚለውን ውሳኔውን በመቃወም ነው።
Source: Link to the Post