የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃና እጀባ ያሰለጠናቸውን 113 ፖሊሶች አስመረቀ

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃና እጀባ ያሰለጠናቸውን 113 ፖሊሶች አስመረቀ

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሁርሶ የመከላከያ ሠራዊት ማሰልጠኛ ማዕከል ለመጀመሪያ ግዜ በከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃና እጀባ ያሰለጠናቸውን 113 ፖሊሶች አስመረቀ።
የምረቃ ስነ ስርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ በተገኙበት መከናወኑን የሰላምና ጸጥታ ጉዳት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እና የሰላምና ጸጥታ ጉዳት ቢሮ ሀላፊ አቶ ናስር ዩያ የእንካን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ከእለቱ የክቡር እንግዶች የተዘጋጀላቸውን ሽልማትና ሰርተፍኬት ተቀብለዋል።

The post የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃና እጀባ ያሰለጠናቸውን 113 ፖሊሶች አስመረቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply