You are currently viewing የሕልውና ዘመቻው ዳርቻ ሕዝባችንን ከዳግም ሰቆቃ መጠበቅ እንጂ በየምዕራፉ እየቆመ የመከራ አዝመራ የሚወቃበት ዐውድማ እንዳይሆን ተገቢው ጥንቃቄ እንዲወሰድ ሲል እናት ፓርቲ አሳሰበ። አማራ ሚ…

የሕልውና ዘመቻው ዳርቻ ሕዝባችንን ከዳግም ሰቆቃ መጠበቅ እንጂ በየምዕራፉ እየቆመ የመከራ አዝመራ የሚወቃበት ዐውድማ እንዳይሆን ተገቢው ጥንቃቄ እንዲወሰድ ሲል እናት ፓርቲ አሳሰበ። አማራ ሚ…

የሕልውና ዘመቻው ዳርቻ ሕዝባችንን ከዳግም ሰቆቃ መጠበቅ እንጂ በየምዕራፉ እየቆመ የመከራ አዝመራ የሚወቃበት ዐውድማ እንዳይሆን ተገቢው ጥንቃቄ እንዲወሰድ ሲል እናት ፓርቲ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተቀስቅሶ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈውንና የአማራና አፋር ክልሎችን ለአሥርት ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰው ጦርነት በሕዝባችንም ላይ ለመስማትና ለማየት የሚዘገንን መከራ ማድረሱን ጠቅሷል፡፡ ትሕነግም ፋታ ሲያገኝ፣ እድሜና ጊዜ ሲገዛ ይበልጥ አጥፊ፣ ይበልጥ ነውረኝነት የሚጠናወተውና እኩይነትን እንደ ካባ የሚደርብ እንጂ ከስህተቱ የሚማር ቡድን እንዳልሆነ የተረጋገጠ ስለመሆኑ ነው እናት ፓርቲ የገለጸው፡፡ ስለሀገር እና ስለወገን ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የከፈሉ ጀግና የወገን ጦር አባላት ክብር እንደሚገባቸው ገልጧል። በዚህ ታሪካዊ የሀገርን ሕልውና የመታደግ ትልቅ ተግባር ለተሳተፉ የጸጥታ ኃይሎችም ፓርቲው ያለውን አክብሮትና ምሥጋና አቅርቧል። ሆ ብሎ ለነጻነቱ በወጣውም ሕዝብ ውስጥ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀሩ በተለያዩ መድረኮች ከሀገራዊ መግባባት ጋር ስለ “ድርድር” እየሰነቀሩ እንዳወያዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ መከላከያው የያዘውን ቦታ አጽንቶ እንዲቆይ የተወሰነው ለወታደራዊ ስልት እንጅ ልክ እንደ ሰኔ 2013ቱ ውሳኔ ፖለቲካዊ ከሆነ ትርፉ ካለፈው በብዙ እጥፍ መዘዝ ይዞ መምጣቱ አይቀሬ ነው ብሎታል። ለሽብሩና እኩይ ተግባሩ መደበቂያ ያደረገውን የትግራይ ሕዝብንም “ከአብራክህ የወጡ ስለሆነ ብቻህን ተጋፈጠው” እንደማለት ይቆጠራል፤ ወዲህም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚያስገባና ሌላ ጦስ ይዞ እንደሚመጣ በአግባቡ መረዳት ያሻልም ብሏል። ያ ሁሉ የዜጎች እልቂት፣ የሀብት ውድመት ከደረሰና ነገሮች ሁሉ ከተመሰቃቀሉ በኋላ ድንገት እምር ብሎ ስለድርድር መታሰቡ ሕይወታቸውን መስዋዕት ባደረጉ ጀግኖቻችንና ንጹሓን ዜጎቻችን ላይ እንደመሳለቅ፣ ሕዝብን ካለመረዳት አለፍ ሲልም ከንቀት የሚቆጠር ነው ብለን እናምናለንና የሚመለከተው ሁሉ በሕግ፣ በሥርዓትና በመርኅ እንዲመራ እየጠየቅን ቀጣዮቹን ሀሳቦች መሰንዘር እንወዳለን:_ ፩ኛ . የዚህ ሁሉ የሀገራችን ምስቅልቅል መነሾና ምክንያት የሆነው ትሕነግ ከኹለተኛው የዓለም ጦርነት ፍፃሜ በኋላ እንደሆነው እንደ ናዚ ፓርቲ እና ርእዮተ ዓለሙ መልሶ ሊንቀሳቀስ እንዳይችል በማድረግ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል። ፪ኛ . መከላከያ ሠራዊታችንና ሕዝባዊ ኃይሉ አሁንም በተጠና መንገድ እንቅስቃሴያቸው ሳይገታ የአፋርና አማራ ክልል ነጻ ያልወጡ ቦታዎችን ጨምሮ በአሸባሪው ትሕነግ ቀንበር ሥር ያለውን የትግራይ ሕዝብና መሬትም ነጻ እንዲያወጡ እንጠይቃለን፡፡ ፫ኛ . የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻነቱን ማወጅ እንጂ በየምዕራፉ የሚቆምና ለዳግም ሰቆቃ የሚዳርግን ግብታዊ ውሳኔ እንደማይቀበል ድጋሚ ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ ፬ኛ . የዜጎች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋል ሕግንና ሕግን ብቻ የተከተለ ለመሆኑ ሕግ አስከባሪው አካል እንዲያረጋግጥ ብሎም እጃቸው ወንጀል ውስጥ የሌሉበት ሰዎች እየተጣራ ነጻ የሚሆኑበት አሠራር እንዲፋጠን እናሳስባለን፡፡ ፭ኛ . አሁን ላይ ሀገር በእጅጉ የምትሻውን ሀገራዊ መግባባት ሂደት ከአተረጓጎም ጀምሮ እስከ አተገባበሩ የሚያምታቱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እያሳሰብን ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ለስኬታማነቱ የጦር ግንባሩን ያህል እንድንመለከተውና የበኩላችንን በጎ አስተዋጽዖ አበርክተን እውን ሆኖ እንድናይ ሁሉም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና እገዛ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ በመጨረሻም ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውም ሆነ አስፈጻሚው ነገሮችን ሁሉ በጊዜውና በአግባቡ ብቻ እንዲወጡ እያሳሰብን ሀገራችን ኢትዮጵያ ለምትፈልግብን የትኛውም ዓይነት ግዳጅ አባላትና ደጋፊዎቻችን በድጋሚ ዝግጁነታቸውን እንገልጣለን ነው ያለው እናት ፓርቲ በመግለጫው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply