የሕወሓት ታማኝ ታጣቂዎች ከከፈቱባቸዉ ጥቃት ያመለጡ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባልደረቦች ወደ አማራ ክልል መግባታቸዉን እንደቀጠሉ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

የሕወሓት ታማኝ ታጣቂዎች ከከፈቱባቸዉ ጥቃት ያመለጡ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባልደረቦች ወደ አማራ ክልል መግባታቸዉን እንደቀጠሉ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

የሕወሓት ታማኝ ታጣቂዎች ከከፈቱባቸዉ ጥቃት ያመለጡ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባልደረቦች ወደ አማራ ክልል መግባታቸዉን እንደቀጠሉ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሰሜን ጎንደር ዞን የበየዳ ወረዳ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት እስካሁን ድረስ ከጥቃቱ ያመለጡ 5000 ያክል ወታደሮች በየዳ ገብተዋል። የወረዳዉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለስልጣናት እንዳሉት የወረዳዉ መስተዳድር ለወታደሮቹ ጊዚያዊ ርዳታ እያደረገ አስተማማኝ ቦታ አስፍሯቸዋል። ወታደሮቹ በየዳ የደረሱት ከትግራይ ክልል የተከዜ በረሐን ጨምሮ ረጅሙን ርቀት በእግር ሲጓዙ ሰንብተዉ ነዉ። ባለፈዉ ጥቅምት 24 የትግራይ ልዩ ኃይል፣ሚሊሺያና ከሰሜን ዕዝ ያፈነገጡ የጦሩ ባልደረቦች ድንገት ከከፈቱባቸዉ ጥቃት ያመለጡ ከአንድ ሺሕ በላይ ወታደሮች ከዚሕ ቀደም አማራ ክልል ዋግ ሕምራ ዞን ሰቆጣ መግባታቸዉን ባለፈዉ ሳምንት ዘግበን ነበር። በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር በሕወሓት ታጣቂዎች ታግተዉ የነበሩ 1000 የሰሜን ዕዝ መኮንኖችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ መንግስት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች ትናንት ዘግበዋል። መገናኛ ዘዴዎቹ የመከላከያ ሚንስቴር መግለጫን ጠቅሰዉ እንደዘገቡት የሕወሓት ታጣቂዎች አንድ ብርጌድየር ጄኔራልን ጨምሮ ባለፈዉ ጥቅምት ያገቷቸዉን 1000 ከፍተኛና መስመራዊ መኮንኖችን አዴት በተባለዉ የቀድሞ የሕወሓት ወታደራዊ ማዘዢያ ጣቢያ ሸሽገዋቸዉ ነበር። የኢትዮጵያ ጦር መኮንኖቹን ያስለቀዉ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ በከፈተዉ ዘመቻ ስለመሆኑ የDW ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply