የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ – ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና፤ የተጀመረው ለውጥ፣ ተሰፋዎቻችን እና ፈተናዎቹ 

ቅዳሜ፣ ሐምሌ(July) 28 ቀን 2018

ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና፤ የተጀመረው ለውጥ፣ ተሰፋዎቻችን እና ፈተናዎቹ   

በቤልጅየምና አጎራባች አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚያሳትፍ እና በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት፣ የወደፊት ተስፋዎቻችንን እና ፈተናዎቹን የሚቃኝ፣ እንዲሁም በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቀውን ድጋፍና ትብብር በሚመለከት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የግማሽ ቀን የውይይት መድረክ ነው። በዚህ አቢይ ስብሰባ ላይ በቤልጅየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተገኝተው የለውጡን ሂደትና እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች በሚመለከት ንግግር የሚያደርጉና ከተሳታፊዎችም ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ስለሆነ በዚህ በአይነቱ የመጀመሪያው በሆነው ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንዲሳተፉ ድልድል፤ በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የውይይት መድረክ ጋብዞዎታል።

የክብር እንግዳ እና የመወያያ ሃሳብ አቅራቢዎች

  1. ክቡር አምባሳደር እውነቱ ብላታ…….  የክብር እንግዳ
  2. ዶ/ር ነገደ ጎበዜ ———————- የውይይት ሃሳብ አቅራቢ
  3. ያሬድ ኃይለማርያም —————— የውይይት ሃሳብ አቅራቢ

 

ቅዳሜ፣ ሐምሌ(July) 28 ቀን 2018

ከቀኑ 13፡00 ጀምሮ

ቦታ፡ ብራስልስ፣

Chaussée d’Anvers  208 /Antwerpsesteenweg 208

1000 Bruxelles

ለተጨማሪ መረጃ. +32.475.275.433/+32.484.781.604/+32.486.336.367 ይደውሉ

Leave a Reply