የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል በጥቂቱ፡-

  • በኮሪደር ልማቱ በታቀፉ አካባቢዎች በዝቅተኛ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ለከፋ ችግር እንዳይዳረጉ እና በተሻለ ሁኔታ ለማቋቋም ምን እየተሰራ ነው፤ የኮሪደር ልማቱ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲስፋፋስ ምን ታቅዷል?
  • የኢትዮጵያ አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ በዋና ዋና አመላካቾች ምን ደረጃ ላይ ነው ?
  • የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን ከመቀነስ አንጻር እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል መንግስት ምን አቅዶ እየሰራ ነው?
  • ማንኛውም የመንግስት አገልግሎት የሚገኘው በእጅ መንሻ ሆኗል፤ ታዲያ መንስግት ይህን ለመፍታት ምን እየሰራ ነው? በጥቅሉ የመንግስታዊ ሌብነት እና የሙስና ችግሮችን ለመፍታት ምን ታቅዷል?
  • በቅርቡ ከቀረበው የኦዲት ሪፖርት ጋር ተያያዞ ብዙ ተቋማት የሃብት ብክነት እየታየባቸው ነው፤ መንግስት ይህን ከመፍታት አንጻር ምን እየሰራ ነው?
  • የአዋሽ ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ የባቡር መንገድ ከመልሶ ግንባታ አኳያ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

በአሁኑ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply